Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0112 730842
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200 ብር (ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Categories Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋሉ፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋሉ፡፡

  1. (ሎት 1) የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቆች
  2. (ሎት 2) የተለያዩ የቢሮና የጽህፈት መሳሪያዎች የተለያዩ የፕሪንተር እና የፎቶኮፒ ቀለሞች ተዛማጅ ዕቃዎች
  3. (ሎት 3) ህትመት
  4. (ሎት 4) የተለያዩ የህክምና መርጃ ዕቃዎች
  5. (ሎት 5) የተለያዩ የትምህርት ዕቃዎች
  6. (ሎት 6) የተለያዩ የጽዳት እቃዎች
  7. (ሎት 7) የተለያዩ መሳሪያዎች (የጥገና እቃዎች)
  8. (ሎት 8) ቋሚ እቃዎች ስለመግዛት ይፈልጋል

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. የአቅራቢዎች ዝርዝር በህጋዊነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ናሙና/ሳምፕል ለሚጠይቁ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው ዕቃዎችን በትምህርት ቤቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በመግለጽ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በሶስት ወይም በአራት በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 09 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ከሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ፣ በጽ/ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱት ምርት ብቻ ከሆነ ልዩ አስተያየት ይደረጋል፡፡
  11. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመገኘት የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
  • (ሎት 1) - 15,200 (አስራ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ብር)
  • (ሎት 2) - 5,900.00 (አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር)
  • (ሎት 3) - 1,800.00 (አንድ ሺህ ስምንት መቶ ብር)
  • (ሎት 4) - 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • (ሎት 5) - 1,100.00 (አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር)
  • (ሎት 6) - 13,000.00 (አስራ ሶስት ሺህ ብር)
  • (ሎት 7) - 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
  • (ሎት 8) - 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ጠ /ሲፒኦ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ አምጥተው ቢሮ ቁጥር 09 ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  1. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  2. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  3. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ካኦ ጂጂ ዱቄት ፋብሪካ ፊት ሰፊ ስፍራ ስልክ ቁጥር 0112 730842/0112 730825/0112 730824

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for purchasing goods across 8 lots: uniforms/sports gear, office supplies, printing, medical aids, educational items, cleaning supplies, maintenance tools, and fixed assets. Bidders need valid trade license, TIN, VAT registration, and supplier registration; samples may be required.
Save Tender