Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ህዳሴ አንደኛ እና መካከስኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 0111-11-52-84/011-1-52-50
  • Website
  • Deadline31 Aug 2026, 5:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceበሎት 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ)
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening dateበ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30
  • Categories Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather

በጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 07 አስተዳደር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዳሴ የአንደኛ መካከለኛ ደረጃ /ት/ቤት በ2019ዓ.ም በጀት በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ህዳሴ አንደኛ እና መካከስኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

በጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 07 አስተዳደር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዳሴ የአንደኛ መካከለኛ ደረጃ /ት/ቤት በ2019ዓ.ም በጀት በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የደንብ ልብስ እና ስፌት ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃ ሎት 3. የህትመት ሥራዎች ሎት 4. አላቂ የሕከምና እቃዎች ሎት 5. የትምህርት መርጃ ሎት 6. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች ሎት 7. ልዩ ልዩ መሣሪያ እና መጽሐፍት ሎት 8. ለሕንፃ፤ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ዕድሳት እና ጥገና ሎት 9 ፕላንት፤ ለማሽነሪ እና ለመሣሪያ ዕድሳት እና ጥገና ሎት 10. ቋሚ የቢሮ እቃዎች ሎት 11 ለመስተንግዶ (የካፌ ኪራይ፣ የምግብ ዝግጅት) ሎት 12, የመኪና ኪራይ የመሳሰሉትን ለመግዛት በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና ምዝገባ ምስክር ወረቀት::
  2. በዘርፉ የተሰማሩበት ፍቃድ በዕቃ አቅራቢነት እና አገልግሎት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገበ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tim) እና የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  3. ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ ለተጠቀሱት እቃዎች የማይመለስ በሎት 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000205510129 (የውስጥ ገቢ) በመክፈል ከባንክ የከፈሉበትን ደረሰኝ በማምጣት የጨረታ ሰነዱን ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  4. በገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች /በዘርፉ የተሰማሩበት/ የተመዘገቡ መሆንዎትን የሚገልፅ ሰነድ መያዝ ይኖርብዎታል ፡፡
  5. ጨረታውን መወዳደር የሚችሉ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ እሴት የሚጨምሩ /አምራች/ ሆነው ከአደራጃቸው ተቋም በሚፃፍላቸው ደብዳቤ መሠረት ያለከፍያ መጫረት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን አሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ አለበት፡፡
  7. ተወዳዳሪዎች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ከጨረታው መከፈቻ ቀን በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች አንድ (1 %) አጠቃላይ ዋጋ ለሎት 1. ብር 15,832 (አስራ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ሁለት ብር ብቻ) ለሎት 2. ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 3. ብር 1500.00(አንድ ሺህ አምስት መቶ ብቻ ለሎት 4. ብር 900.00 (ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ) ለሎት 5. ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 6. ብር12000.00 (አስራ ሁለት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 7. ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) የጨረታ ለሎት 8. ብር 17390.00 (አስራ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና) ለሎት 9.ብር2700 (ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ብር ብቻ) ለሎት 10. ብር 10,890 (አስር ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና) ለሎት 1 ብር 13,833.00 (አስራ ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ሦስት ብርብቻ) ለሎት 12. ብር 5760.00 (አምስት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ብር ብቻ) ዋስትና ቢያንስ ለስድስት ወር ፀንቶ የሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ ከዋና ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ድረስ የሚቆይ ሲሆን በ10 ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ውል ከመፈረማቸው በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ት/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እቃዎች ካለው በጀትና (የተሻለ መንገድ ካገኘ) እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የዕቃዎችን 20% መቀነስ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፡- ጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 7 ከሰሜን ማዘጋጃ ከፍ ብሎ ከላዛሪት ት/ቤት ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111-11-52-84/011-1-52-50 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

በጉስሴ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ህዳሴ አንደኛ እና መካከስኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of goods and services across 12 lots, including uniforms, office supplies, printing, medical items, educational materials, cleaning supplies, equipment, books, renovation works, vehicle rental, and catering. Bidders must hold a renewed trade license, VAT registration, and supplier registration.
Save Tender