Tender Detail

Tender Details

  • Company የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ባለው መንገድ ገባ ብሎ ሼህ ሆጀሌ መስጊድ አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112305111
  • Website
  • Deadline31 Aug 2026, 5:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 100.00 (አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት 1፡- 16,000 ብር፣ ሎት 2፡- 20,000 ብር፣ ሎት 3፡- 10,000 ብር፣ ሎት 4፡- 24,000 ብር፣ ሎት 5፡- 34,160 ብር፣ ሎት 6፡- 23,232.00 ብር ሲሆን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/
  • opening dateበ11ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Ict Equipment'S And Its Accessories

የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን ሎት 1፦ የደንብ ልብስ ማገዢ የደንብ ልብስ ስፌት እና የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት 2፡- የፅህፈት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የትምህርት አላቂ ዕቃዎች ለመዋዕለ ህፃናት የሚያገለግሉ የትምህርት ዕቃዎች የመጀመሪያ ህከምና መርጃ ዕቃዎች፤ ለቤተ-ሙከራ የሚያስፈልጉ ኬሚካሎች እና ዕቃዎች ለስፖርት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች፣ ሎት 3፡- የዕዳት ዕቃዎች እና የህትመት ስራዎች፣ ሎት 4፡- ጥገና (የኮምፒውተር የፕሪንተር ፎቶኮፒ እና ማባገዢያ ማሽኖች) የውሃ ቧንቧ መስመር ጥገና፣ የኤሌከትሪክ መስመር ጥገና የበርና መስኮት ጥገና ዴስኮች የቢሮ ፓርቲሽን ስራ የግቢ ቴራዞ ንጣፍ ስራ ከነአቅርቦቱ፣ ሎት 5፡- የኤሌክትሮንክስ ግዢ (ኮምፒውተር፣ ላፕ ቶፕ ፕሪንተር እና ሴኪውሪቲ ካሜራ እና ከነገጠማው ላሚኔተር እስካነር)፣ ሎት 6፡- የሰራተኞች መስተንግዶ ግዢ እነዚህን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በየዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የተዘጋጀው ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት ሎት 1፡- 16,000 ብር፣ ሎት 2፡- 20,000 ብር፣ ሎት 3፡- 10,000 ብር፣ ሎት 4፡- 24,000 ብር፣ ሎት 5፡- 34,160 ብር፣ ሎት 6፡- 23,232.00 ብር ሲሆን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ በቀለም አምባ ቅ/አ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሲፒኦ/CPO/ ያላስያዘ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ውስጥ ያስረክባል፡፡
  6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል በት/ቤቱ የዕለት ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ በመሙላት ለዚህ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ የማያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. የጨረታ ሣጥን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
  10. የጥቃቅንና አነስተኛ ልዩ አስተያየት የሚያገኙት ባመረተው ምርት እና በምርቱ ላይ እሴት በጨመሩት ብቻ ሲሆን ሌሎች እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው CPO አስይዘው ይወዳደራሉ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ት/ቤቱ የዕቃዎቹን ብዛት 20% የመጨመር /የመቀነስ/ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ መሆንዎ ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% CPO በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ፡- ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስትያን ፊት ስፌት ባስው መንገድ ገባ ብሎ ሼህ ሆጀሴ መስጊድ አጠገብ
ስልክ:- 0112-30-41-55

የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement across six lots: uniforms, textiles, sports gear; office/school supplies, lab chemicals; furniture and printing; maintenance works; electronics (computers, printers, cameras); and staff hospitality items. Bidders must hold valid licenses, TIN, VAT registration, and submit samples.
Save Tender