Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት በሄራዊ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ግዥ አስተዳደር ቡድን
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 0111 11 83 94 /0111 11 70 50 70
  • Website
  • Deadline31 Aug 2026, 5:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/
  • Bid Securityለሎት 1፥ 2000 /ሁለት ሺህ/ ሎት 2፥ 2000 /ሁለት ሺህ/ ሎት 3፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 4፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 5፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 6፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 7፥ 2000 /ሁለት ሺህ/ ሎት 8፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 11፥ 3500 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ/ ሎት 12፥ 3500 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Food And Beverage , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብሄራዊ ቤተመንግስት ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የ2019 ዓ.ም የአስራ አንድ ዙር በጀት ዓመት ግዢ የሚያስፈልገውን እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት በሄራዊ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ግዥ አስተዳደር ቡድን


ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብሄራዊ ቤተመንግስት ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የ2019 ዓ.ም የአስራ አንድ ዙር በጀት ዓመት ግዢ የሚያስፈልገውን እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የደንብ ልብስ ሎት 2. የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 3. አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 4. ህትመት ሎት 5. ህክምና ሎት 6. የት/ት እቃዎች ሎት 7. የጽዳት እቃዎች ሎት 8. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት 9. የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 10. የጭነት አገልግሎት ሎት 11. ፕላንት እና ማሽነሪ ሎት 12. ቋሚ እቃዎች ሎት 13. ምግብ እና መጠጥ ናቸው።

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ዋጋቸውን ቫትን ጨምሮ በኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፣
  5. የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የጨረታውን ሰነድ በነፃ ይወስዳሉ ከአደራጃቸው ተቋም ወቅታዊ የሆነ በአድራሻችን የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያና ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ለሎት 1፥ 2000 /ሁለት ሺህ/ ሎት 2፥ 2000 /ሁለት ሺህ/ ሎት 3፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 4፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 5፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 6፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 7፥ 2000 /ሁለት ሺህ/ ሎት 8፥ 3000 /ሶስት ሺህ/ ሎት 11፥ 3500 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ/ ሎት 12፥ 3500 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብሄራዊ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን አንደኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ሸሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን /የስራ ቀን/ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብሄራዊ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒው ተለይቶ በፖስታ ላይ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብና ሌሎችንም ዕቃዎች በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሠረት ዋጋቸውን በአግባቡ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  12. ናሙና ያልቀረበበት እና የዘገየ በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም ከጨረታ ሠነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣
  13. ተጫራቾች 10% ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  14. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  15. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚቀርብበት ዕቃ ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት ዕቃ ከገበያ ላይ ገዝተው ለሚወዳደሩት እያንዳንዱ ምርት ዕቃ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም፤
  17. መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

አድራሻ- ናዘሬት ት/ቤት ወረድ ብሎ
ስልክ ቁጥር- 0111 11 83 94 / 0111 11 70 50 70

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብሄራዊ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን

✨ messages.ai_summary
Open tender for procuring goods across 13 lots, including clothing, tailoring, office supplies, printing, medical, educational, cleaning, equipment, transport, freight, plant/machinery, fixed assets, and food/beverage. Bidders must have valid tax clearance, renewed trade license, TIN, VAT registration, and supplier registration.
Save Tender