የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ
አከይ ኦንፎ ዴፋቮሪዜ የተባለው አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
አከይ ኦንፎ ዴፋቮሪዜ የተባለው አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ተጫራቾች
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት የድርጅቱ ንብረት ባለበት ግቢ በመገኘት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት እና በአስራ አምስተኛው ቀን 7፡30 ሰዓት ድረስ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች መመልከት ይችላል።
- ተጫራቾች የሚገዙትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በድርጅቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ አስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፤ የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
- አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ እና በ7 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር እየከፈሉ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ ከድርጅቱ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግቢ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 09 11 67 63 13 / 09 55 99 21 87/ 09 39 66 58 04/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- ኮተቤ ካራ መሳለሚያ ልዩ ስሙ ዘርፌ ቦኖ መቅደስ ግሮሰሪ ወረድ ብሎ
አከይ ኦንፎ ዴፋቮሪዜ
✨ messages.ai_summary
A local charity organization is selling various used items via open auction, as-is. Bidders can inspect items at the premises, must submit a 20% bank-guaranteed CPO, and purchase tender documents for 200 birr. Winning bidders must pay within 5 days and collect items within 7 days.
