የጥበቃ እና የጽዳት ሰራተኞች ዩኒፎርምና ጫማዎች ግዥ
ሎያል ሴኩሪቲ አ/ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
ለሎያል ሴኩሪቲ አ/ማ ለጥበቃ እና ለጽዳት ሰራተኞች አልባሳትና ጫማ ግዥ
ሎያል ሴኩሪቲ አ/ማ ለ2019 ዓ/ም የስራ ዘመን አገልግሎት የሚውሉ የጥበቃ ሰራተኞችና የጽዳት ሰራተኞች ዩኒፎርምና ጫማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. የሚገዙ እቃዎች
- የጥበቃ ሱሪ
- የጥበቃ ሸሚዝ
- የጥበቃ ኮት
- የጥበቃ ጃኬት
- የጽዳት ሰራተኛ ሽርጥ
- ኮፍያ
- ከረባት
- የሴት ጉርድ ጫማ፣ የወንድ ጉርድ ጫማ፣ ቦት ጫማ እና ጉርድ ቦት ጫማ
2. ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች:-
- በዘርፉ የሚሰሩ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ቲን ነምበር፣ ቫት ተመዝጋቢ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ሰነድ በተወሰነው ዋጋ መግዛት የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ bid security/ በባንክ ጋራንቲ /CPO /50,000.00/ሃምሳ ሺህ/ብር ማስያዝ የሚችል
- የቀረበለት የአልባሳትና ጫማዎች የተጠየቀውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለና ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል፡፡
3. የጨረታ ሂደት:-
- የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 300 ብር በመግዛት በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ዋናው ቢሮ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እስከ 11፡00 ሰአት ድረስ መውሰድ ይቻላል፡፡
- ጨረታው ከ5ቀን በኋላ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ሰአት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ አ/አ/ከ/አስ/ቦሌ ከ/ከ ወረዳ03 ቦሌ መድሀኒያለም ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢ/ቁ 213ኤ ስልክ 0974181910/ 0913331349/ 0928603774 ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሎያል ሴኩሪቲ አ/ማ
✨ messages.ai_summary
Procurement of uniforms and footwear for security and cleaning staff: trousers, shirts, coats, jackets, caps, ties, shoes, and boots. Bidders need a valid trade license, TIN, VAT registration, certificate, and tax clearance, and must meet quality standards.
