Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address አጠና ተራ ከድልድዩ ከፍ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112739821
  • Website
  • Deadline19 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00 ብር (ለእንድ ሎት)
  • opening dateበዛው ቀን ከጠዋቱ 4:30
  • Categories Food And Beverage , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

አጠቃላይ የአላቂ እቃ እና አገልግሎት ግዥ


1ኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡- አ/ከ/ክ/ከ/ወረዳ 12 ፋይናንስ ግዢ/ዋ/ስ/ሂ/የጨ/ቁ-002/2019

የአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት 1ኛ ዙር ለሚያከናውነው አጠቃላይ የአላቂ እቃ እንዲሁም አገልግሎት ግዥ የዝግጅት ምዕራፉን አጠናቆ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የእቃና አገልግሎት ግዥ መደቦች ላይ ተቋሙ ያስቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል፡፡

ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያና አላቂ እቃዎች----------------------------CPO (2%)
ሎት 2 የዕዳት እቃዎች-------------------------------------------CPO (2%)
ሎት 3 የደንብ ልብስ----------------------------------------------CPO (2%)
ሎት 4 CPO------------------------------------------------------- (2%)
ሎት 5 የሰራተኛ ምግባ--------------------------------------------CPO (2%)
ሎት 6 የመኪና ጎማ እና እቃዎች---------------------------------------CPO (2%)
ሎት 7 የስፖርት እቃዎች-------------------------------------------CPO (2%)
ሎት 8 ዲኮር-------------------------------------------------------CPO (2%)
ሎት 9 መስተንግዶ-------------------------------------------------CPO 10,000.00
ሎት 10 ትራንስፖርት-----------------------------------------------CPO 10,000.00
ሎት 11 ኤሌክትሮኒከስ ጥገና--------------------------------------CPO 10,000.00
ሎት 12 ፈርኒቸር ጥገና---------------------------------------------CPO 10,000.00
ሎት 13 የህትመት ስራዎች-----------------------------------------CPO 10,000.00
ሎት 14 የግብርና ግብአት እቃዎች----------------------------------CPO 10,000.00
ሎት 15 የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት-----------------------------CPO 10,000.00

መስሪያ ቤታችን ከላይ በተገለፀው የግዥ መደብ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ወይም አቅራቢን አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
  2. የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
  3. የዘመኑን ግብር የከፈለበት ክሊራንስና ህጋዊ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው
  4. የጨረታ ሰነዱ ሙሉ እያንዳንዱ ገፅ ተሞልቶ ተፈርሞ ማህተም ተደርጎበት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መመለስ አለበት /ይህን ሳያደርግ የጨረታ ሰነዱን ለሚመልስ ነጋዴ ከጨረታው ውድድር ውጪ እንደሚሆኑ እናሳውቃለን፡፡

ከላይ ከተራቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ኮልፌ አጠና ተራ መናፈሻ ፊት ለፊት የተቋሙ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በሚገኘው ፋይናንስ ፅ/ቤት በግንባር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 ብር (ለእንድ ሎት) በመከፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል ከላይ በተገለፀው መሰረት ከሎት 1-7 የሚያቀርቡትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% እንዲሁም ከሎት 8-14 ደግሞ 10000.00 /አስር ሺ ብር/ ህጋዊ CPO በተቋማችን ስም አስርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከመዋዋላቸው በፊት ያሸነፉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ህጋዊ CPO በማሰራት ለጨረታ ውል ማስከበሪያነት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ሙሉውን በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ ብለው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጫራች የሚሞላውን ከፍል በጠቅላላ ሞልተው ፈርመው ማህተም አድርገው የጨረታ መቀበያ ቀነ ገደቡ ሳያልፍ ለዚሁ ስራ ተብሎ በፅ/ቤቱ ግዥ ከፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት የመጠቀሚያ ጊዜው ቢያንስ 1 ዓመትና ከዛ በላይ የሆነ እና በሳምፕሉ መሰረት አድርገው ወረዳው ንብረት ከፍል ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለጥቃቅንና አንስተኛ ተወዳዳሪዮች የጨረታ ማስከበርያ አስተያየት የምናደርገው ለሚያመርቱት ምርት ብቻ እሱንም በደብዳቤ የምናስተናግድ መሆነ እንገልፃለን፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን በትህትና እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም እረፍት ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን በትህትና እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- ኮልፌ አጠና ተራ ኮልፌ ፓርክ ፊት ለፊት ወይም ቁጠባ ሰፈር ጀርባ ወደ ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን/ሎሚ ሜዳ በሚወስደው መንገድ 200 ሜ. ወደ ግራ ገባ ብሎ ለበለጠ መረጃ በ0118278077/0910584301 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ፋይናንስ ፅ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- Open tender by the Addis Ketema Sub-city Woreda 12 Administration Finance Office (Addis Ababa) for the general procurement of consumable goods and services across 15 lots, covering office stationery, food items, uniforms, employee meals, vehicle tires, sports equipment, décor, hospitality, transport, electronics and furniture repair, printing, agricultural inputs, and tailoring services. - Bid documents cost 300.00 ETB per lot (non-refundable) and are available for 10 consecutive working days from the announcement date; bids must be submitted by the 11th day at 4:00 AM and will be opened the same day at 4:30 AM. - Bid security is 2% of the total offered price for lots 1–7 and a 10,000.00 ETB legal CPO for lots 8–15; winning bidders must also provide a 10% legal CPO as contract security. - Eligibility requires a valid renewed business license, business registration, VAT and supplier registration certificates, current-year tax clearance, and a fully completed, signed, and stamped bid document; samples must be submitted for the items being bid.
Save Tender