ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎች ግዢ
በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የጎሎልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር-ጎወ/1/2019
በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የጎሎልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር የጽህፈት መሣሪያዎች የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ያላቸው እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 2000 (ሁለት ሺህ) እንዲሁም ለጽዳት እቃዎች ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) በጽ/ቤቱ ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000075143797 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በእናት ፖስታ ላይ ሙሉ ስማችሁን ሙሉ አድራሻችሁን የድርጅቱ ማህተም፡ስልክ ቁጥር እና ፊርማ የግድ መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎሎለልቻ ወረዳ አስተዳደር አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም፣ ለጽዳት እቃዎች ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15000 (አስራ አምስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኘው የታወቀ ባንክ በከፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ አይነት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ አቅምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ጫንጮ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (0910319050) (0912313241) (0912289754) ይጥይቁ።
በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የጎሎልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The Arsi Zone Finance Office, Gololcha District Finance Office invites bids for permanent office items, electronic furniture, stationery, cleaning supplies, employee uniforms, and vehicle tires. Bids must be submitted by the 16th working day at 4:00 (morning), with opening the same day at 4:30. Bid document prices are ETB 2,000 for office items, electronics, furniture, and stationery, and ETB 1,500 for cleaning supplies, uniforms, and tires; bid bonds are ETB 20,000 and ETB 15,000 respectively (payable by CPO only). Bidders must have a renewed trade license, current tax payment, VAT registration, tax identification number, supplier registration, and must submit samples.
