Tender Detail

Tender Details

  • Company ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት የባሴ ትሪ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ
  • Address አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, Phone: 0911 127265
  • Website
  • Deadline18 Aug 2026, 12:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00
  • Bid Securityብር 50,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ11 ቀን ቆይቶ በ 12 ኛው ቀን 03፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ 61 ሰው የሚጭን ፊያት N3 ዘመኑ ያለፈበት ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ ባለበት ሁኔታ ማህበሩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት የባሴ ትሪ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ


ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ህዳር 02 ቀን 1957 ዓ.ም. የተቋቋመ ቢሆንም ማህበሩ ከ1966 ዓ.ም. ጀምሮ በንግድ ስራ ላይ አለመኖሩን ሰነዶች ያመለክታሉ። በአባላቱ ለፍርድ ቤት በቀረበ አቤቱታ ማህበሩን እንደገና ለማደራጀት ያልተቻለ በመሆኑ ሁኔታውን ለአባላቱ ቀርቦ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተደረገ መደበኛ እና አስቸኳይ የአባላት ስብሰባ በአባላቱ አብላጫ ድምጽ ማህበሩ እንዲፈርስ ተወስኗል።

በዚህም መሰረት የማህበሩ ሂሳብ የማጣራት ስራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

በሂሳብ ማጣራቱ ሂደትም ከማህበሩ አባላት በቀረበ ጥያቄ መሰረት የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር ንብረት የሆነ 61 ሰው የሚጭን ፊያት N3 ዘመኑ ያለፈበት ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ በባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ ይገኛል።

በመሆኑም ይህን ንብረት ባለበት ሁኔታ ማህበሩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከላይ የተዘረዘረውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 በባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር ስም በተከፈተው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ አ.አ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ከማህበሩ ቢሮ ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

1)     ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በራሱ ወጪ ባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ በመገኘት መመልከት የሚችል።

2)     በጨረታው ለመሳተፍ ብር 50,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም በማህበሩ ስም የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር በተከፈተው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ ማስያዝ የሚችል።

3)     በጨረታው አሸናፊ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ /ድርጅት በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመክፈል ንብረቱን ሙሉ በሙሉ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ በራሱ ወጪ እና ኃላፊነት ማንሳት የሚችል።

4)     የጨረታ ሰነዱ መሰረት የሚገዛበትን ዋጋ እና የጨረታ ዋስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም ባንክ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ሰነድ በአንድ ላይ በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን አ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመገኘት ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚችል።

5)     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት የሚዘጋ ይሆናል፡፡ ጨረታው በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 ይከፈታል።

6)     ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7)     ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 531 3167 / 09 11 12 72 65 (አቶ ዘሪሁን ደጀኔ) ወይንም 09 11 67 99 69 (አቶ ንጉሴ) በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።

ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት

የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ

✨ messages.ai_summary
- Third announcement for the sale of a 61-passenger Fiat N3 bus, an outdated vehicle parked for many years and intended for spare-parts use, located in Bale Goba at Haji Mohammed Ahmed Salah compound. - Issued by Zemedhun Adane Certified Audit Firm, auditor of Bale Transport, Cattle, Trade and Development Share Company (under liquidation). - The tender is open for 10 consecutive days from publication, closes on the 11th day at 6:00, and is opened on the 12th day at 3:00 at Keker Building, 5th Floor, Office 506, Mexico area, Addis Ababa. - Bid document price: non-refundable 500 ETB; bid bond: 50,000 ETB payable via bank-confirmed CPO or deposit to Awash Bank account number 01322240761900. - Bidders may inspect the asset at their own cost in Bale Goba; the winner must pay in full within 5 days of award and remove the asset within 10 days at their own responsibility and expense.
Save Tender