ክርስቲያን በጎ አድራጎትና ማህበራት ህብረት (ሲሲአርዲኤ)/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ለማህበረሰብ በጎ ፈቃደኞች የሚውሉ 6,700 የካንቫስ ቦርሳዎችን ለማምረትና ለማቅረብ ብቃትና ልምድ ያላቸውን አቅራቢዎች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
Christian Relief And Development Association ( CCRDA )
የካንቫስ ቦርሳ ግዥ
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ማህበራት ህብረት (ሲሲአርዲኤ)/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ለማህበረሰብ በጎ ፈቃደኞች የሚውሉ 6,700 የካንቫስ ቦርሳዎችን ለማምረትና ለማቅረብ ብቃትና ልምድ ያላቸውን አቅራቢዎች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. የግዥው ዝርዝር
- የዕቃው ዓይነት፡ የካንቫስ ቦርሳ (Canvas Bag)
- ብዛት፡ 6,700
- በቦርሳው ላይ ሲሲአርዲኤ/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት እና የአጋር ድርጅቶች አርማዎች እንዲሁም ከበጎ ፈቃደኝነትና ከፕሮግራሙ ጋር የተያያዘ መልዕክት ጥራት ባለው ቋሚ ቀለም መታተም አለበት።
- ዝርዝር ቴክኒካል መመዘኛ (Specification) በጨረታ ሰነዱ መሠረት ይሆናል።
2. ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገቡ መስፈርቶች
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
- የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (TIN/VAT እንደአግባቡ)፤
- ተመሳሳይ ሥራ የማከናወን ልምድ ያለው መሆኑን የሚገልጥ ማስረጃ፤
- የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛል ማቅረብ፤
- የተጠናቀቀ የቦርሳ ናሙና (Sample) ማቅረብ።
3. የማስረከቢያ ጊዜ
አሸናፊው ተጫራች ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ 25 ቀናት ውስጥ ሙሉ ትዕዛዙን አጠናቆ ማስረከብ አለበት።
4. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ
- ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ (ToR) ከሲሲአርዲኤ መ/ቤት በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበቅ ቀን ጀምሮ ቢሮ ቁጥር 304 በመገኘት መውሰድና መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የቴክኒክ ፕሮፖዛል፣ የፋይናንስ ፕሮፖዛል፣ የሥራ ዕቅድ እና የተጠናቀቀ ናሙና በታሸገ ፖስታ ለሲሲአርዲኤ/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ቢሮ፣ ቢሮ ቁጥር 304 እስከ ማክሰኞ ነሐሴ 12 ቀን 2026 እስከ 10፡30 ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
5. ማሳሰቢያ
- የአርማዎች ፋይልና የህትመት መልዕክት በሲሲአርዲኤ/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ይቀርባል።
- የቀረበው ናሙና ከተፈቀደ በኋላ የብዛት ምርት ይጀምራል።
- (ሲሲአርዲኤ)/ኮር ግሩፕ ፓርትነርስ ፕሮጀክት ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ጨረታዎች የመቀበል ወይም ያለምንም ምክንያት የመሰረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ – 0911427891/00911643937
