Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወልድያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
  • Address AMHARA Ethiopia, Phone: 0993360439
  • Website
  • Deadline17 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2026-08-17 10:30:00
  • Categories Vehicle tire

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ የወልድያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ቤት ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሴሪያል ቁጥር ያላቸው ያገለገሉ ጎማወችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወልድያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ የወልድያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ቤት ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሴሪያል ቁጥር ያላቸው ያገለገሉ ጎማወችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ከላይ በተዘረዘሩት የጨረታ ሂደቶች ላይ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች፦

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆነዎ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቸው እንዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡

2. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ከ25/11/2018 እስከ 10/12/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ 300 ሶስት መቶ/ብር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ወልድያ በሚገኘው በጥገና ጽ/ቤቱ ግዥ/ፋ/ን/አ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያውን የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼከሲፒኦ/ ለመ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡

4. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆነዎ የሚያረጋግጥ የዋናውን ፎቶ ኮፒ በማያያዝ በፖስታ አሽገው እስከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በጥገና ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ካወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታና በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የድርጅትዎን ማህተምና አድራሻ ፊርማ በማድረግ ለመስሪያ ቤቱ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ጨረታው 11/12/2018 ዓ.ም 4:00 ስዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ የተሟላ ከሆነ ይከፈታል::

7. ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎች ላይ ሁሉንም በጠቅላላ ዋጋ (በሎት) የሚሞላ መሆኑ የታወቅ፡፡

8. አሸናፊ ተጫራቾች ከታወቀ በኋላ ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንከ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች በጨረታው ግምገማ ውጤት ቅሬታ ካላቸው ውጤቱ በተገለጸበት በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

10. ጥገና ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ያወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡

11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ ከሰአት እሁድ ወይም የባአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡

12. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በ0993360439 ይደውሉ፡፡

 

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወልድያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት

Save Tender