የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በሚያስተዳድረው በቁጥር አንድ ሕንጻ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ፎቅ የሚገኘውን ቦታ ለተለያዩ ሕጋዊ አገልግሎቶች ለቢሮ፣ ለባንክ፣ ለትምህርት ተቋማት፣ ለድርጅቶች እና ለመሳሰሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በሚያስተዳድረው በቁጥር አንድ ሕንጻ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ፎቅ የሚገኘውን ቦታ ለተለያዩ ሕጋዊ አገልግሎቶች ለቢሮ፣ ለባንክ፣ ለትምህርት ተቋማት፣ ለድርጅቶች እና ለመሳሰሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ሕጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስም ማዘጋጀት የሚችሉ ሲሆን የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ከሆነ ከጨረታ ውጭ የሚያደርግ በመሆኑ ሙሉ አድራሻና የሚከራዩበት የዋጋ ዝርዝር ግልፅ ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒቨርሲቲው ገንዘብ ቤት 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 010 የጨረታውን መመሪያና ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺ ብር ብቻ/ ከፍሎ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ሕንጻ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነድ ማስገባት ይቻላል፡፡
4. ቦታው በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ፣ የቤተ ከርስቲያኒቱንና የዩኒቨርሲቲውን ክብር፣ ሥነ-ምግባርና ደኅንነት የማይጋፋ የሥራ ዘርፍ ያላቸው (ለሃይማኖታዊና የሥነ-ምግባር እሴቶች ተገዢ የሆኑ)፡፡
5. የቤቱ የካሬ ሜትር መጠን እና የጨረታ የመነሻ ዋጋ ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
6. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁትር +251111233529 +251910586066 011-8-121605
ወይም በዩኒቨርሲቲው ሕንጻ አስተዳደር ቢሮ በአካል ቀርበው ይጠይቁ
ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ
