Tender Detail

Tender Details


አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ ያገለገሉ  ኮምፒውተሮች ፣ፕሪንተሮች ፣ስካነሮች፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ በሮች  ፣መስታወቶች  ፣የበር እና መስኮት ፍሬሞች ፣ፋይል ካቢኔቶች፣ጎማዎች፣ የእንጨት መደርደሪያዎች  እና ሌሎችም  እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Aggar Micro Finance S.C


ያገለገሉ ዕቃዎች ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ ያገለገሉ  ኮምፒውተሮች ፣ፕሪንተሮች ፣ስካነሮች፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ በሮች  ፣መስታወቶች  ፣የበር እና መስኮት ፍሬሞች ፣ፋይል ካቢኔቶች፣ጎማዎች፣ የእንጨት መደርደሪያዎች  እና ሌሎችም  እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ

ተጫራቾች  ንብረቶቹን ቃሊቲ ሞኤንኮ  ጋራዥ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ ከሰኔ8/2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ16/2018ዓ/ም ድረስ  በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ ፡፡

ተጫራቾች የ2018 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ  እና  የታክስ ከፋይነት  ማረጋገጫ  ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድ ማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ /በመክፈል  መውስድ  ይችላሉ፡፡

ጨረታው ሰኔ17/2018ዓ/ም  ከጠዋቱ 4 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4.30  በኩባንያው ዋና መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት  አይቻልም ፡፡

ተጫራቾች ለሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ ማስከበሪያ 15% /አስራ አምስት በመቶ/ በአጋር ማይክሮ ፋይናንስ ስም  በባንክ ክፍያ ማስያዣ /CPO/  ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው  ከብር 1000.00 /አንድ ሺ/ ብር ማነስ የለበትም፡፡

የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን  ዋጋ  ላይ  ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ 15% በተጨማሪነት ይከፍላል፡፡

አሸናፊው የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ  ባለው  10 የስራ ቀናት  ውስጥ ክፍያ ፈፅመው  ንብረቶቹን ካላነሣ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለኩባንያው  ገቢ ይሆናል ፡፡

ኩባንያው የተሸለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

                                                    አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ/ማ

                                ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ  ዳማስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 308

                               ስልክ ቁጥር  251-11-5577195  ፋክስ 251-11-5577234

                                                       አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Save Tender