የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት የመኪና መለዋወጫ ዕቃወች: የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የቢሮ እቃወች ፡ቁርጥራጭ እንጨቶች የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፡የተለያዩ አይነት ቶነሮች፡ያገለገሉ የመኪና ባትሪ፤የተለያዩ ጀሪካኖች ፤ለስላሳ መጠጦች፤ቬንትሌተሮች፤ ያገለገሉ በሮች፤በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
Ethiopian Red Cross Society (ERCS)
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶች የግልፅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት የመኪና መለዋወጫ ዕቃወች: የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የቢሮ እቃወች ፡ቁርጥራጭ እንጨቶች የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፡የተለያዩ አይነት ቶነሮች፡ያገለገሉ የመኪና ባትሪ፤የተለያዩ ጀሪካኖች ፤ለስላሳ መጠጦች፤ቬንትሌተሮች፤ ያገለገሉ በሮች፤በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ወይም የ2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያደሱ ፣እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፣ የግብር መለያ ሰረትፍኬት እና በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አንዱ ተጫራች በሌላዉ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚያሳግድ ይሆናል፡፡
- ተጫራቶች ከጨረታዉ በኃላ የሚመለስ የጫረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ለሚጫረትበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር አምስት (10) የስራ ቀናት ውስጥ ጨረታ ሰነዱን በጉርድ ሾላ ሳህሊተ ምህረት ቤ/ክያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት የጨረታዉን ዝርዝር መረጃ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ በብር (800) ብር (ስምንት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ ሰኔ 16 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጃዉ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ባቀረባዉ ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘዉ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም፡፡
- የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት የሚፈልጉ ሳህሊተ ምህረት ቤ/ክያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘዉ የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር ግምጃቤት በመገኘት ጨረታው በሪፓርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ሰኔ 16 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 በጉርድ ሾላ በሚገኘዉ ሳህሊተ ምህረት ቤ/ክያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘዉ የማህበሩ መሰብሰቢያ አደራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ክፍያው (5) በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስረከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰዉ አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የእትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
ስልክ ቁጥር፡ 011-515-06-08
ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ 41076
