ኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አክሲዮን ማኅበር አንድ (1) FORD E-350 ሞዴል በጥሩ አቋም ላይ ያለ ፎርድ አምቡላንስ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
International CRDO
የጨረታ ማስታወቂያ (ለጋዜጣ የተላከ)
የጨረታ ቁጥር፡ ……..…………….
ኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አክሲዮን ማኅበር አንድ (1) FORD E-350 ሞዴል በጥሩ አቋም ላይ ያለ ፎርድ አምቡላንስ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ተሸከርካሪው የተሠራበት ዘመን እ.ኤ.አ 2009፣ በናፍጣ የሚሠራ፣የሞተር ፈረስ ጉልበት 184፣ የሞተር 6000 ሲሲ ፣ ስምንት ስሊንደር እና አንድ አክስል ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዶች፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አ.ማ. ፋይናንስ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሠባት (7) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጧቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ እንድሁም ቅዳሜ ከጧቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የብቃት መስፈርት፡
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ሠርቲፍኬት ከግብር ከፋይ መለያ ሠርቲፍኬት ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አ.ማ. ስም ጨረታው ፀንቶ ለሚቆይባቸው ለተጨማሪ 28 (ሃያ ስምንት) ቀናትን የሚሸፍን ብር50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ መክፈቻ፡ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት በ8ኛው (ስምንተኛው) ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማኅበሩ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ባለው የመሰብሰቢያ አደራሽ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0116678646 ወይም 0116678552 መደወል ይቻላል፡፡
- አክሲዮን ማኅበሩ ሌላ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፣ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፡ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 3፣ የቤት ቁጥር አዲሰ፡ ፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ወደ አቤም ሆቴል መሄጃ መንገድ ላይ አይ ሲ ኤም ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ነው፡፡
