ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አክስዮን ማህበር በድርጅቱ የሚገኙን ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Buusaa Gonofaa Microfinance S.C
የጨረታ ማስታወቂያ
ቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ
ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አክስዮን ማህበር በድርጅቱ የሚገኙን ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጠመንጃ ያዥ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪየ ቤታችን በቤተ ሰኢዳ ህንጻ 4ኛ ፎቅ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ቢሮ በመምጣት የጨረታውን መረጃ ፤ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መወሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት መጋዘን እና ሞጆ በሚገኘው ቅርጫፍ ጽ/ ቤታችን በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡ የኮምፒተር እና ፕሪንተር እቃዎች የሚገኙት በዋናው መ/ቤት ንብረት ክፍል ሲሆን የተቀሩት እቃዎች የሚገኙት ሞጆ በሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዜያዊ መጋዘን ውስጥ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለያንዳንዱ ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20% ( ፐርሰንት) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤምቬሎፕ በማድረግ በድርጅታችን የንብረት ክፍል ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ( ሲፒኦ) እንዲሁም በጨተታው የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለጸውን የጨረታ ማከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፤ በ10ኛው ቀን ማለትም ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በድርጅታችን የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጫረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፊዎች ዝርዝር በመስሪያ ቤቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ3 /ሶስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 / ሁለት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስረከቢያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከድርጅቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርባችዋል፤፤ ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ላልፈረሙ ወይም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከቢሪያ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፤፤
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው ወጭ በማጓጓዝ ውል በተፈረመ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተማላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ድርጅቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኘውም ተጫራች ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈከገ በስልክ ቁጥር 0114 162536 ፤ 0936784833 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውንም ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ምድብ1. የኮምፒተር እና ፕሪንተር እቃዎች
| ተ.ቁ | የእቃዉ አይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1. | የኮምፒዩተር ሞኒተር | በቁጥር | 9 |
| 2. | የኮምፒዩተር ኪ ቦርድ | “ | 25 |
| 3. | ኤችፒ ሌዘርጄት ፕሪንተር | “ | 14 |
| 4. | ዴስክ ቶፕ ሲ ስተም ዩኒት | “ | 23 |
| 5. | ላፕ ቶፕ ኮምፒተር | “ | 20 |
| 6. | የኮምፒዩተር ስፒከር | “ | 8 |
| 7. | የኤች ዲ ኤም አይ ገመድ | “ | 2 |
| 8. | ኮፒ ማሽን ካኖን 2202 | “ | 1 |
| 9. | የዉሃ ማጣሪያ | “ | 2 |
| 10. | ጠረጴዛ የኮፒ ማሽን ማስቀመጫ | “ | 1 |
ምድብ2. ጀነሬተሮች
| ተ. ቁ. | የእቃው ዓይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1 | ካማ ጀነሬተር | ቁጥር | 3 |
| 2 | ሮቢን ጀነሬተር | ቁጥር | 5 |
ምድብ 3. ፌሮ ብረት እና ብረታ ብረት እቃዎች
| ተ. ቁ. | የእቃው ዓይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1 | የብረት መስኮት ባለ መስታወት | በቁጥር | 2 |
| 2 | የብረት በር ባለ መስታወት | በቁጥር | 1 |
| 3 | የመስኮት ፍርግርግ ብረት | በቁጥር | 1 |
| 4 | ፌሮ ብረት ( ባለ 10፤ እና ባለ 12) | በቁጥር | 29 |
| 5 | የአጥር ሽቦ ባለ እሾህ | በጥቅል | በጥቅል |
| 6 | የውሃ ቱቦ ብረት | በቁጥር | 4 |
| 7 | ስታፋ ብረት | በጥቅል | በጥቅል |
| 8 | ያረጁና ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች | በቁጥር | |
| 9 | ታፔላ ብረት | በቁጥር | 2 |
| 10 | የብረት በር | በቁጥር | 3 |
| 11 | የብረት መስኮት | በቁጥር | 1 |
| 12 | አሮጌ ቱቦላሬ | በቁጥር | 14 |
| 13 | የከተም በር | በቁጥር | 1 |
ምድብ 4. ፕላስቲክ ነክ እቃዎች
| ተ. ቁ. | የእቃው ዓይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1 | ፕላስቲክ ቆርቆሮዎች | በቁጥር | 2 |
| 2 | ፒፒሲ ጆይንት ባለ 110 | በቁጥር | 11 |
| 3 | ፒፒሲ ሙሉ | በቁጥር | 4 |
| 4 | ፒፒሲ ½ (ግማሽ) | በቁጥር | 4 |
| 5 | የኮርኒስ መስሪያ ፕላስቲኮች | በቁጥር | 15 |
ምድብ 5. እንጨት እና እንጨት ነክ እቃዎች
| ተ. ቁ. | የእቃው ዓይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1 | የእንጨት መስኮት | በቁጥር | 3 |
| 2 | የእንጨት መስኮት ባለ መስታወት | በቁጥር | 2 |
| 3 | የእንጨት መስኮት ባለ ፌሮ ፍርግርግ ብረት | በቁጥር | 1 |
| 4 | የእንጨት በር | በቁጥር | 8 |
| 5 | የእንጨት ሞራሌ | በቁጥር | 3 |
| 6 | ጣውላ | በቁጥር | 1 |
| 7 | የተሰባበሩ እንጨቶች | በቁጥር | 8 |
አድራሻ፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ቤተ ሰኢዳ ህንጻ 4ኛ ፎቅ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ (አ.አ.) ስልክ ቁ. 0114 162621 /0936784833
