Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Bank of Ethiopia
  • Address P. O. Box 255, Addis Ababa, Ethiopia, Tel. 251-11-372-28-72, 251-11-372-28-26., Phone: 251-11-372-28-72
  • Website
  • Deadline29 May 2026, 5:14 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-29 17:14:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial Bank of Ethiopia


የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ. ቁ
የተበዳሪ ስም
የንብረቱ አስያዥ ስም
የይዞታው አይነት/ የሚሰጠው አገልግሎት
አድራሻ
የይዞታው

ስፋት (ካ.ሜ)

የባለቤትነት መታወቂያ ቁጥሩ
የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)
ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት
1.
አቢሲኒያ የቄራ አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ
ምንተስኖት የእንጨት እና የብረታብረት ስራ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
ቅይጥ ተግባር ያለዉ መጋዘን
በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ቀበሌ 03
2200
302/2007
40,723,428.03
21/09/2018 ዓ.ም

3፡00-4፡00 ጠዋት

2.
አቢሲኒያ የቄራ አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ
ኪሩቤል ተሾመ
ለኢንደስትሪ አገልግሎት የሚዉል መጋዘን
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ሰበታ ከተማ ቀበሌ 04
3000
L/2868/2002
23,351,132.11
21/09/2018 ዓ.ም

4፡00-5፡00 ጠዋት

3.
ሸኮ አሞራ ገደል የቡና አምራች ገበሬዎች ሁለገብ ኃ/የተ/ኅ/ሥራ ማህበር
ተበዳሪው
የቡና መፈልፈያ ድርጅት
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ መሀል ሸኮ ቀበሌ
28,350
527/33/2014
4,214,686.25
21/09/2018 ዓ.ም

5፡00-6፡00 ጠዋት

 በመሆኑም፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡
  2. ጨረታዉ የሚከናወነዉ አምባሳደር አካባቢ በሚገኘዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 42ኛ ፎቅ በሚገኘዉ አዳራሽ ቁጥር 4203 ነው፡፡
  3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡
  4. ለጨረታ ከቀረቡ የመኖሪያ ቤቶች ዉጪ የሆኑ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡
  6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡፡
  7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
  9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡                                  

ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ. 011-113-05-08 ወይም አምባሳደር አካባቢ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት 42 ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Save Tender