Tender Detail

Tender Details

  • Company Hibret Bank
  • Address , Phone: 011 470 6541
  • Website
  • Deadline19 May 2026, 11:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-19 12:00:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች የተመለከተውን ተሸከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

Hibret Bank


የሐራጅ ማስታወቂያ

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች የተመለከተውን ተሸከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

የተበዳሪ ስም የአስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ የሰሌዳ ቁጥር የተሽከርካሪ አይነት የስሪት ዘመን የሻንሲ ቁጥር የሞተር ቁጥር የሐራጅ መነሻ ዋጋ(ተጨማሪ ዕሴት ታክስ አይጨምርም) ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
 

ኤ.ጂ.ኢ. የግንባታ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማ/

አቶ ዘካርያስ አብዱልሰመድ አህመድ ጅማ ኢት-03-87241 ደረቅ ጭነት- ቻይና ሲኖትራክ 2016-እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር LZZ5BLNF5GN138452 WD615.47*161007019697*

 

7,295,652.00 ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት
አቶ ዘካርያስ አብዱልሰመድ አህመድ ጂማ ኢት-03- 26388 ተሳቢ- ኢትዮጵያ ደረቅ ጭነት 2016-እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር EAUBDAKMEG0000016 – ·         1,573,913.00

 

ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ተሽከርካሪውን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡ተሽከርካሪው ላይ ቀረጥ ተከፍሎበታል፡፡
  3. ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ንብረት ለሚገዛና  የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  4. የተሽከርካሪው ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  5. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ናቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  7. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  8. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  10. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ መረጃ የሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114 70 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
Save Tender