ፀደይ ባንክ አ.ማ ለጃን ሜዳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በደብረ ብርሃን ከተማ የካርታ ቁጥር ደብኢፓ /03/0020/2014 የቦታዉ ስፋት 20000 ካ ሜ የሆነ የኢንዱስትሪ ሸድ እና ቦታ ለፕሌይ ዉድና ኤምዲኤፍ ማምረቻ አገልግሎት የሚዉል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Tsedey Bank S.C
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለጃን ሜዳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በደብረ ብርሃን ከተማ የካርታ ቁጥር ደብኢፓ /03/0020/2014 የቦታዉ ስፋት 20000 ካ ሜ የሆነ የኢንዱስትሪ ሸድ እና ቦታ ለፕሌይ ዉድና ኤምዲኤፍ ማምረቻ አገልግሎት የሚዉል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል፡፡
- የቤቱ የጫረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ግምቱ 116,435,020.15 (አንድ መቶ አስራ ስድሰት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ዜሮ ሃያ ብር ከአስራ አምስት ሳንቲም የሆነ
- ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል፡፡
- በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት፡፡
- የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
- በጫረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል/፡፡ ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
- ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላና ፍላጎት ላለዉ ተጫራች በሚሰጠዉ ከፍተኛ ዋጋ ባንኩ እስከ 30% ( ሰላሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- ጫረታዉ የሚካሄደዉ ሰኔ 2/2018 ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6.00 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ
በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251918779825 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
