Tender Detail

Tender Details

  • Company Public Servants Social Security Administration (የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር)
  • Address ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋናው መ/ቤት አጠገብ ዋስትና የንግድ ማዕከል ግራውንድ ላይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-11-23-13
  • Websitehttps://psssa.gov.et/
  • Deadline17 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-17 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅን ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ለቢሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቤት በተጠቀሱት ክ/ከተሞች ውስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

Public Servants Social Security Administration (የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር)


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-PSSSA/AAR/03/2018

 

በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅን ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ለቢሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቤት በተጠቀሱት ክ/ከተሞች ውስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

1.     የቤቱ ሁኔታ ቪላ ወይም ፎቅ ሆኖ ቢያንስ 500 ካሬ ሜትር እና ከዚያ በላይ የመገልገያ ወለል ስፋት ያለው ክፍል/ክፍሎች ሆኖ በተጠቀሰው ካሬ ስፋት ውስጥ ወይም በፎቁ መካከል በተከራይ የተያዘ ክፍል የሌለው መሆኑ አለበት።

2.     ቤቶቹ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌና ለሚኩራ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ መሆን አለባቸው።

3.     ቤቱ ፎቅ ከሆነ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ውሃና የኤሌክትሪክ መስመሮች የተዘረጉለት እና እንደ አስፈላጊነቱ የሊፍት አገልግሎት እየሰጠ ያለ መሆን አለብት።

4.     ቤቱ ራሱን የቻለ ግቢ ቢኖረውም ባይኖረውም ቢያንስ ሁለት መኪና ማቆሚያ ቦታ ያለውና በቂ መፀዳጃ ቤት ያለው መሆን አለብት።

5.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና ፕላን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

6.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አሥር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ ከሚገኘው የሪጅኑ ጽ/ቤት ዋስትና ህንፃ ግራውንድ ላይ በመምጣት የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

7.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሠነድ በመሙላት ከላይ በተራ ቁጥር 6 ላይ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ ሠነዱን በገዙበት የሪጅኑ ጽ/ቤት የጨረታ ሠነዱን አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8.     የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ ልክ 3፡00 ሰዓት የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት 3፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።

9.     መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. 11ኛው ቀን የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

 

አድራሻ፡- ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ ዋስትና የንግድ ማዕከል ግራውንድ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ቁጥር፡- 011-1-11-23-13

 

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅን

Save Tender