የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል ቀጥሎ የቀረቡትን እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት አርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ
የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል ቀጥሎ የቀረቡትን እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
• የህንፃ መሳሪያ እቃዎች
• ማሽነሪዎች
• የፈርኒቸር እቃዎች
ሲሆን መ/ቤታችን ጨረታውን የሚያከናውነው የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ እና የግዥ አፈፃፀም መሠረት በግልጽ ጨረታ ስነ - ስርዓት ሆኖ ለውድድሩ የሚጋበዙት
ተጫራቾች
1. በሙያው ዘርፍ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው እና ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
3. አቅራቢዎች ለሚጫረቱበት እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 /አስር ሺ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረ /CPO/ ከኦርጅናል ሠነድ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. የእቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበትቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን
6. የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን መ/ቤቱ በሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ በሚለው ቦታ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ ዋጋ በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተም በኦርጅናልና በኮፒ ፖስታ ላይ በማድረግ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል ሆኖም 16ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
8. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመኖራቸው የጨረታውን መክፈቻ አያስተጓጉልም፡፡
9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ማዕከሉ የማምጣትና የማስረከብ ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የስልክ ቁጥር፡- 0468811883/0468810564/0913820570
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት አርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል
