Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር/ጤ/ጽ/ቤት ወረዳ 03 የመሪ ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ/ም የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

አዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር/ጤ/ጽ/ቤት


የግዢ ጨረታ መለያ ቁጥር 002/2018ዓ/ም

 

በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር/ጤ/ጽ/ቤት ወረዳ 03 የመሪ ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ/ም የሁለተኛ ግማሽ ዓመት በግልፅ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት እቃች ሎት - 1 የደንብ ልብስ ፣ ሎት - 2 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ ሎት - 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት - 4 የህትመት ስራዎች ፣ ሎት - 5 አላቂ የህክምና ዕቃዎች ፣ ሎት - 6 ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣ ሎት - 7 የጥገና እቃዎች & ሎት- 8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች መ/ቤቱ ባወጣው እስፔስፍኬሽን መሰረት ሎት- 9 ቋሚ የህክምና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች

1.       ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2.       በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3.       የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣

4.       የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5.       በማንኛዉም ግልፅ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት ፡፡

6.       ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ C.PO. ማቅረብ አለባቸው።

ሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

 

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ

 

ሎት 1

 

የደንብ ልብስና ስፊት

 

ብር 10,000.00

 

ሎት 2

 

አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች

 

ብር 10,000.000

 

ሎት 3

 

የጽዳት ዕቃዎች

 

ብር 10,000.00

 

ሎት 4

 

የህትመት ስራዎች

 

ብር 10,000.00

 

ሎት 5

 

አላቂ የህክምና ዕቃዎች

 

ብር 10,000.00

 

ሎት 6

 

ልዩ ልዩ ዕቃዎች

 

ብር 6,000.00

 

ሎት 7

 

የጥገና ዕቃዎች

 

ብር 10,000.00

 

ሎት 8

 

በቋሚ የቢሮ እቃዎች

 

ብር 20,000.00

 

ሎት 9

 

ቋሚ የህክምና እቃዎች

 

ብር 20,000.00

 

 

7.       የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 51 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

8.       ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር /ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ በመሪ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 55 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላቦትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9.       ጨረታው በ11ኛው ቀን ካጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን አና በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10.   ተጫራቾች ላሸነፉባቸዉ ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።

11.   ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው በተጨማሪም በፎቶ በማንዋል/ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።

12.   በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

13.   መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

14.   መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡_ እያንዳንዱ ዋጋ ሲሞላ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ/ክ/ከ/ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ አያት አደባባይ አለፍ ብሎ ወደ አራብሳ

በሚወስደው አስፓልት ዞን 5ት መንገድ 12 በኮሮኮንች መግቢያ መንገድ 1500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

ስልክ ቁጥር 0910513885

 

አዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር/ጤ/ጽ/ቤት

Save Tender