Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለማሻ ወረዳ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለማሻ ወረዳ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

•        ሎት 1ኛ፡- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

•        ሎት 2ኛ፡- ፈርኒቸር ዕቃዎች

•        ሎት 3ኛ፡- የጥገና ሠራተኞች ደንብ ልብስ

•        ሎት 4ኛ:- የቪዲዮ ካሜራዎች ከነ አክሰሰሪው

ተጫራቾችም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ማሟላት የሚችሉትን ተጫራቾችን ይጋብዛል

1)     በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለውና የ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና ተጨማሪ የእሴት ታከስ ተመዝጋብ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት

2)     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸዉ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ከኢት/ያ ንግድ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡

3)     ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) ብር ከማሻ ወረዳ ገ/ባ/ሥ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) መውሰድ ይችላሉ።

4)     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

5)     ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት (አራት) ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በ16ኛው ቀን የመንግሥት ሥራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግሥት የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡

6)     የጨረታው አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎቹን አጓጉዞ በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።

7)     ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፡፡

8)     መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0967012681 ወይም 0912789043 ወይም 0925270431 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender