በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የወረዳ 4 ገላን ቁ.1 የመ/መ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለአገልግሎት ላይ የሚውል ደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል
በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የወረዳ 4 ገላን ቁ.1 የመ/መ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የወረዳ 4 ገላን ቁ.1 የመ/መ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለአገልግሎት ላይ የሚውል እቃ ግዥ
ማለትም፡-
ሎት 1 ደንብ ልብስ ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት 3. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ሎት 5 የጽዳት ዕቃዎች ሎት 6 የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች
በዚሁ መሰረት፡-
1. ተጫራቾች በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ። ተጫራቹ በማንኛውም መንግስት መ/ቤትም ሆነ በግል ድርጅት በጨረታ ምክንያትም ይሁን በሌሎችም ያልታገደና ያልተከሰሰ መሆን አለበት።
4. የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት እና ቅዳሜን ጨምሮ በት/ቤቱ ግዥ አስተባባሪ ቢሮ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ10ኛዉ ቀን ልክ 11.00 ተዘግቶ በ11ኛዉ ቀን ልክ 4.30 ላይ የሚከፈት ሲሆን 11 ቀን ቅዳሜ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ሰኞ በተባለው ሰዓት ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ለመከፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ (ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ) ብቻ ለአንድ እቃ አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል። ለአንድ አቃ 2 አይነት ናሙና ያቀረበ ተጫራች ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ይገለላል። በተጨማሪም ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው አና በመረጠው ናሙና መሰረት ግዥው ይፈፀማል፡፡ በተጨማሪም ውስብስብ አይደሉም ልዩ ግምገማ አያስፈልጋቸዉም ብሎ መስሪያ ቤቱ ያመነባቸዉን እቃ በዋጋ በማወዳደር ግዥ ይፈጸማል።
8. ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ብቻ 2% cpo ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቹ በሁለት ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ብቻ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሁለት ኤንቨሎፕ ውጪ የቀረበ ሰነድ ከጨረታዉ ሙሉ በሙሉ ይገለላል።
9. ተጫራቾች በተጫራቾች የሚሞላውን በከፍል አራት ላይ የሚገኘውን ማንኛዉም መረጃ በጥንቃቄ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሳይሞሉ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ዉድቅ ይደረጋሉ።
10. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉት ዕቃ መጠን የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ይህን ጨረታ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ካላቸዉ ግለሰቦች ጋር የሚመሳጠር የጨረታ ሰነዱን ለማሻሻል ለመቀየር እንዲሁም የሌላኛውን ተጫራች ዋጋ መሰረት በማድረግ መሙላት እና ዋናው የጨረታ ሰነድና ኮፒ በየትኛዉም አግባብ የማይመሳሰል ከሆነ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም በፍሉድ የተነካካ ከሆነ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑና የጨረታ ማስከበሪያው cpo እንደሚወረስባቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም አንድ ተጫራች ሊወዳደር የሚችለው በአንድ ድርጅት ብቻ ሲሆን በተለያየ ድርጅት ተወዳድሮ ከተገኘ ሙሉ በሙሉ ከውድድሩ ይገላል።
12. የጨረታው ዋጋ የሚሞላው በተቀመጠለት መለኪያ ብቻ ሲሆን ከመለኪያው ውጭ የተሞላ ዋጋ ውድቅ ይደረጋል።
13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅተው ለሚመጡ ተጫራች ከአደራጃቸው ወረዳ የድጋፍ ደብዳቤ በተደራጀበት ዘርፍ ጠቅሶ ማምረት በሚችሉት ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ።
15. ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተጠቀሱትን ያላሟላ ከሆነ በቀጥታ ከውድድሩ ዉድቅ ይደረጋል።
16. ጨረታ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድም ሆነ ናሙና ተቀባይነት የለውም
17. ለሀገር ውስጥ ምርት ቅድሚያ እንሰጣለን።
18. የጨረታ ውጤት በውስጥ ማስታወቂያ የሚለጠፍ ሲሆን ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልግ ተጫራች ውጤቱ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 7 ተከታታይ የስስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላል። ነገር ግን በጽሁፍ ያልቀረበ ቅሬታ ተቀባይነት የለውም።
አቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ወረዳ 4 ገላን ቁ.1 የመ/መ/ ደ/ ት/ቤት
አድራሻ፡- ገላን ኮንዶሚኒዬም ታከሲ ተራ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ
በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የወረዳ 4 ገላን ቁ.1 የመ/መ/ደ/ት/ቤት
