የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የአካባቢ እና የግል ንጽህና መጠበቂያ ግብዓት ለሚሰሩ ማህበራት ሥራ ማስጀመሪያ እና ለሴቶች የወር አበባ ጊዜ የግል ንጽህና ጤና መጠበቂያ ዕቃ ግዥ ሎት 1፡-እጅ መታጠቢያ ዕቃ ግዥ ሎት 2፡-ሞዴስ መስፊያ ማሺን/MHEH Pad sewing machine/ ሎት3፡- ሞዴስ መስፊያ ጨርቅ/cotton fabrique/ዕቃ ሎት 4፡-አሸዋ እና ጠጠር ግዥ ከዚህ በታች በቀረበ
SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የአካባቢ እና የግል ንጽህና መጠበቂያ ግብዓት ለሚሰሩ ማህበራት ሥራ ማስጀመሪያ እና ለሴቶች የወር አበባ ጊዜ የግል ንጽህና ጤና መጠበቂያ ዕቃ ግዥ ሎት 1፡-እጅ መታጠቢያ ዕቃ ግዥ ሎት 2፡-ሞዴስ መስፊያ ማሺን/MHEH Pad sewing machine/ ሎት3፡- ሞዴስ መስፊያ ጨርቅ/cotton fabrique/ዕቃ ሎት 4፡-አሸዋ እና ጠጠር ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት መጫረት የሚችሉት፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ታክስ ክሊራንስ የቲን ተመዝጋቢና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ10/ አስር/ ተከታታይ ቀናት ለዚህ ጉዳይ በተዘጋጀ ዝርዝር መግለጫዎች የያዘ ሠነድ (specification) በመግዛት መጫረት ይችላሉ።
3. የጨረታ ሰነድ ላይ በመፈረም እና የድርጅታችሁን ማህተም በማሳረፍ ለየሎቱ ዕቃ በዋጋ ሰነድ ላይ ዋጋ በመሙላት ቫትን ያካተተና ያላካተተ ስለመሆኑ በመግለፅ በማሳወቅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ11ኛው ቀን ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግ/ከ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ጨረታው 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም። ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ስም በባንክ በተረጋገጠ CPO በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
6. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል የጨረታ ዶከመንት ለየብቻ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. የጨረታ ዋስትና ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
8. ጨረታው ለ3 ወራት/90 ቀናት/ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
9. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ግዥ/ክ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የግዥ ክፍል ቁጥር 27 ማገኘት ይቻላል።
10. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 046 212 6783
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
