የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (inflight catering) ለስካይላይት ሆቴል እና ለሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፓስታ እና መካሮኒ ምርቶች ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሶሥት (3) ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: - SSNT-T607
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (inflight catering) ለስካይላይት ሆቴል እና ለሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፓስታ እና መካሮኒ ምርቶች ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሶሥት (3) ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡- በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፊቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣ አንድ (1) ዓመትና እና ከዛ በላይ የሰራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T607 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል እስከ ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር: 011-517-4552
ብርቱኳን ሰሙ
ኢ-ሜይል: birtukans@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
