Tender Detail

Tender Details

  • Company መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር
  • Address ሲዳሞ ተራ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112-31-31-47
  • Website
  • Deadline20 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-20 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር መርካቶ ላይ ባሠራው የገበያ ማዕከል ውስጥ ለልዩ ልዩ አገልግሎት/ለሱቅ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት/ የሚውል ቦታን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር


ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል የሕንፃ ቦታ ኪራይ ጨረታ

 

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር መርካቶ ላይ ባሠራው የገበያ ማዕከል ውስጥ ለልዩ ልዩ አገልግሎት/ለሱቅ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት/ የሚውል ቦታን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት፡-

1.     ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 7 ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በአክሲዮኑ የባንክ ሂሳብ ገቢ በማድረግ መርካቶ ሲዳሞ ተራ የማኅበሩ ሕንፃ በሚገኝበት 4ኛ ፎቅ ላይ ዘወትር በሥራ ቀናት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

2.     ጨረታው በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡

3.     ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 (ሰባት) ቀናት አክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር M433 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት በ7ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ በ4፡45 ሰዓት ይከፈታል፡፡

አክሲዮን ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0112-313147/0112-313237/0118-722926 ወይም በአካል ሲዳሞ ተራ መተሳሰብ የገበያ ማዕከል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

Save Tender