Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በ18 ሉኳንዳ ወደ አሸዋ ሜዳ በሚወስደው መንገድ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112592157
  • Website
  • Deadline09 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-09 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Educational And Training Equipment And Machinery

በኮልፌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጨረታ ማስታወቂያ 003/2018ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኮልፌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጨረታ ማስታወቂያ 003/2018ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በተጫራቾች መመሪያ

1.     ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

❖  1. የደንብ ልብስ፣               2. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች             3. የፅዳት ዕቃዎች

በተጫራቾች መመሪያ

ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2.     ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚሸጡበትን እያንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመግለጽ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ዓይነት በግልጽ በመፃፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የኮልፌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋ/ግ/ን/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 የጨረታ ሳጥን መግባት ይኖርበታል፡፡

3.     ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና፣ ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፣ ሰነዶቹ በማኅተም ማረጋገጥ አለባቸው።

4.     በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት እቃዎችን ከግዥ አስተዳደሩ ጋር በሚገባው ውል መሠረት እንዲያስገባ ሲታዘዝ እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ በራሱ ወጪ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

5.     አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ እቃዎች ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

6.     ማንኛውም ተጫራች የመ/ቤቱ የእቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የእቃዎችን ጥራት አይቶ መ/ቤቱ ካወጣው የጨረታ ሰነድ እና በጨረታው እንዲያልፍ ከተደረገው የእቃ ቴክኒካል ስፔስፌኬሽንና ከቀረበው ናሙና ጋር የማይጣጣም ከሆነና ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ጨረታውን አሸንፎ እቃ እንዲያቀርብ የታዘዘው /ድርጅት/ እቃውን እንዲመልስ ማድረግ ይችላል፡፡

7.     በጨረታው ያሸነፈ አካል ማሸነፉ እንደተገለፀለት ከመ/ቤቱ ጋር በ15 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት ፡፡

8.     የግዥ ውል የሚፈፀምበትን ጊዜ ሰነዱ ላይ የተሰጠው የእቃ ብዛት በተወሰነ መጠንን ሊጨምርም ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት፡፡

9.     ተጫራቶች ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ቀደም ብለው ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ቢሮ ቁጥር 6 ማስረከብ አለባቸው።

10. የሚሸጠው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ መክፈል ይኖርበታል። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ የጨረታ ሣጥኑ ተዘግቶ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይከፈታል።

12. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎቶች የተጠቀሰውን ብር ከታወቀ ባንክ በCPO አሰርታችሁ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

ሎት 1

ሎት 2

ሎት 3

600

1,200

4,000

 

ለበለጠ መረጃ አድራሻ

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በ18 ሉኳንዳ ወደ አሸዋ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ኮልፌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ ይገኛል።

ስልክ ቁጥር/0112592157/011279201

 

የኮልፌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender