በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ በመራኛ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ 2. ፅዳት እቃዎች፣ 3. የኤሌክትሮኒክስ፣ 4. ህትመት፣ 5 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ በመራኛ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ በመራኛ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ 2. ፅዳት እቃዎች፣ 3. የኤሌክትሮኒክስ፣ 4. ህትመት፣ 5 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል። የሚገዙትን እቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ የሚችል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/እንዲሁም በጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 150 /አንድ መቶ ሃምሳ/ ብር በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ መራኛ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ቢን ቦንድ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንከ በተረጋገጠ ቼክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በአዲሱ የንግድ ስራ መስጫ መደቦች እና የተሰማሩበት የንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ ኮድ ቁጥርየንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ መደብ እና የተሰማሩበት የስራ መስኮች በተገለጸው ትንታኔ በተፃፈው ተመሳሳይ ካልሆነ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
5. ተጫራቾች የእቃውን ዋጋ ዝርዝር እና በጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን 3፡30 ሰአት ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ በመራኛ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባለተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት በሚዳ/ ወ/ወ/በመራኛ/ጤ/አጠ/ጣቢያ ግቢ ውስጥ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን በእል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ሆኖ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቹ እቃውን በሚዳ ወረሞ ወረዳ በሚገኘው በመራኛ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች በተቀመጠላቸው ክፍት ቦታ ላይ የእቃውን ሞዴል ብራንድ /መለያ/ የተመረተበትን ሃገር አካቶ ካልሞሉ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ።
9. ተጫራቾች የፕሪንተር ቀለም ናሙና ካላቀረቡ ከወድድር ውጭ ይሆናሉ።
10. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጥራት ያለውና ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0920075661 / ደውለው ይጠይቁ የሚዳ ወረሞ ወረዳ
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ በመራኛ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
