በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 03 ፋ/ጽ/ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አውጥቶ የተለያዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 03 ፋ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ለ/ኩ/ክ/ከ/ወ/03/ፋ-02/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 03 ፋ/ጽ/ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አውጥቶ የተለያዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ
1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የቲንነምበር ሰርተፍኬት እና የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ሎት 1: የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000፣ ሎት 2: ልብስ ስፌት ብር 2,000 ሎት 3: የኪራይ እቃዎች 3,000 በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም የጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ብቻ እንደምርጫቸው በአንዱ ፖስታ በተራ ቁጥር 1 ከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ቢድ ቦንድ አንቀበልም።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ድረስ እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 ብር በመክፈል ሀያት አደባባይ ዙሪያሽ ሞል 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 504 ግዥ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋና፣ ኮፒውን እና በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩትን የቴክኒክ ሰነዶችና ሲፒኦውን ለየብቻው በ3 የታሸገ ኢንቨሎፕ በወረዳው ፋ/ጽ/ቤት G-5 ቢሮ ቁጥር 504 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ማንኛውም መሳተፍ የሚፈልግ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
5. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ግዥ ቡድን በአካል ቀርበው ውል መግባት አለባቸው። አሸናፊዎች ውል ሳይዙ እቃ ጭነው ቢመጡ ወደ መጋዘን ማስገባት አይችሉም።
7. የጨረታ ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊዎች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ እና በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ይገለጻል።
8. በጨረታ ተሳታፊ የሆኑ ድርጅቶች የሚወዳደሩበትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ 3 ቀን ቀድመው ለጽ ቤቱ ማቅረብ አለባቸው። በቢሮ ባሉ ናሙናዎች የተባሉትን ቢሮ ውስጥ ያሉትን ይመልከቱ ፎቶ አንስቶ መያዝም ይጠበቃል።
9. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 011 893 19 09 ግዥ ቡድን ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
10. እያንዳንዱ ሎት ለየብቻ በፖስታ ታሽጎ ይቀርባል የሁሉም ሎት ኮፒ በ1 ፖስታ ማድረግ ይቻላል። አቀላቅሎ ማቅረብ በፍፁም የተከለከለ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ወረዳው ከሀያት አደባባይ ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ ከአደባባዩ 500 ሜትር ዙሪይሽ ሞል ወረዳ 03 አሰተዳደር 5ኛ ወለል ላይ እናገኛለን።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 03 ፋ/ጽ/ቤት
