የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒዬን ሃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ ዕቃዎችን ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር OCFCU/03/2026
የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒዬን ሃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ፡-
1. ሎት-01 ደንብ ልብስ፤
2. ሎት-02 የፅዳት ዕቃዎች፤
3. ሎት-03 የፅሕፈት መሳሪያዎች፤
4. ሎት-04 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች እና
5. ሎት 05 የደንብ ልብስ ማሰፊያ አገልግሎትን ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚታሟሉ ጨረታ ሰነዱን በመግዛት መጫረት ይችላሉ።
1. የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 800.00 (ስምንት መቶ ብር) በኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ (OCFCU) በሚል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000369311747 ወይንም በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000005951163 ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን ደረሰኝ በመያዝ ከዩኒዬኑ ሂሳብ ክፍል (103 ቁጥር) ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አራት (14) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በሥራ ሰዓት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። ቅዳሜ ቀን የሥራ ሰዓት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ብቻ ነው።
2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፤
3. ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
5. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
6. አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
7. የዘመኑ ግብር መክፈሉ እና ክሪላንስ ከ6 ወር በኋላ የተሰጠ ማቅረብ የሚችል፤
8. ተወካይ ከሆነ/ ከሆነች ሕጋዊ የውከልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፤
9. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ጨረታ ሰነዱ በአግባቡ ታሽጎ የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት፤
10. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ቴክኒካል ኦርጅናል ፋይናንስ እና ኮፒዎችን በየብቻቸው በመለያየት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
11. ተጫራች ለሚጫረት ዕቃ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው፤ ነገር ግን የዕቃ መግለጫ (specification) ያላቸው ዕቃዎች ናሙና ለማቅረብ አይገደድም፣
12. የጨረታ ማስታወቂያው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፤
13. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በየሎቱ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ በሚል ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ወይንም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይንም ከኦሮሚያ ባንክ ብቻ በማሰራት በፋይናንስ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
14. የጨረታ መክፈቻ ቀን በተመለከተ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ በዩኒዬናችን 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ሰነዱን በማስገባት እና በዚሁ ቀን በ4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ሆኖም 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፤
15. የተሟላ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
16. ዩኒዬኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ አካባቢ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ገላን ቅርንጫፍ ያለበት ሕንፃ ላይ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0114 45 00 46/ 09 78 60 21 62
የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒዬን ሃላፊነቱ የተወሰነ
