Tender Detail

Tender Details


በን/ስ/ላ/ክ /ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኘው ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢው መለያ ቁጥር 02/2018

 

በን/ስ/ላ/ክ /ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኘው ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት

 

የሎት ዝርዝር

የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O መጠን

ሎት 1 የቢሮ ፅህፈት መሳሪያ

4,000

ሎት 2 ቋሚ እቃዎች

5,000

ሎት 3 የትምህርት እቃዎች

4,000

ሎት 4 ፅዳት እቃዎች

3,000

ሎት 5 የደንብ ልብስ

3,000

ሎት 6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

3,000

 

በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ፡-

1.     በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቶች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2.     ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በየሎቱ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2-02 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2-02 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ11፡30 ታሸጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2-02 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

6.     ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣ ሎት 2፣ ሎት 3 እና ሎት 4 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 2 በቀረበው የተሟላ የፍላጎት መግለጫ መሠረት ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7.     ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

8.     የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

9.     አሸናፊው ተጫራች ውል ገብቶ እቃዎችን ገቢ ከማድረግ በፊት የወል ማስከበሪያ ዋስትና ድበዳቤ ወይም ካሸነፋቸው እቃዎች 10% ማስያዝ ይኖርበታል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ሃይሌ ጋርመንት ሃጫሉ መንገድ ኖክ ማዲያ ጀርባ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 011-4-71-31-90/91

 

ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender