Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር አ/ጤ/ጣ 002/2018 ዓ.ም የጨረታ ቁጥር 002/2018

 

 

ሎት 1 ህትመት፣ ሎት 2 መድኃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ ሎት 3 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣ ሎት 5 ቋሚ ዕቃዎች - ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ግዥዎች መወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።

1.     ለተጠቀሱት ዕቃዎች ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከአቃቂ ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 510 በአካል በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

2.     ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለሚያቀርቡት ዕቃ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ።

3.     ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

5.     ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ለተወዳደሩበት መደብ 1. ለሎት 1 የብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር)፣ 2. ለሎት 2 የብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር)፣ 3. ለሎት 3 የብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር)፣ 4. ለሎት 4 የብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር)፣ 5. ለሎት 5 የብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለትና ተመላሽ የሚሆን ዋስትና ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።

6.     ተጫራቾች በሚወስዱት የመ/ቤቱ ሰነድ ላይ ቫትን ያካተተ ዋጋ በመሙላት ሙሉ ሠነዱ መመለስ አለበት።

7.     በጤና ተቋሙ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ስፔስፊኬሽን በመሰረዝ ማስተካከል አይቻልም።

8.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልጽ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም በሠነዱ ላይ በመምታት ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በተለያ ፖስታ በማድረግ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድነት በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 508 ዘወትር በስራ ሠዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

9.     ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል) ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

10. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የሚያሲዝ ይሆናል።

11. ተጫራቾች በሁሉም በሚጫረቱበት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከ1 (አንድ) ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የማይያዙ ናሙናዎችን ግልፅ በሆነ ፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በሚያቀርቧቸው ናሙናዎች ላይ ከአምራች ድርጅቱ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት ምልክት ወይም የተጫራቹ ማህተም የተደረገበት ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።

12. በካሬ የሚለኩ ግዥዎች ላይ ተጫራቾች ቦታው ላይ በመገኘት መለካት ይኖርባቸዋል።

13. የተሰረዘ፣ የተደለዘ እና ግልፅነት የሌለው የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።

14. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ከተቋሙ የድጋፍ ደብዳቤ እና የአምራችነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- አቃቂ ልዩ ስሙ የድሮው ምክር ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 011 842 03 30

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

Save Tender