Tender Detail

Tender Details

  • Company Abbay Basin Administration Office (አባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት)
  • Address ባህር ዳር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0583216896
  • Websitehttps://aba.gov.et/
  • Deadline02 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-02 00:00:00
  • Categories Laboratory Equipment And Chemicals , Vehicle tire

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Abbay Basin Administration Office (አባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት)


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ.ቤ.አስ.ጽ/01.2/2018

 

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። የጨረታው ሰነድ የሎት (lot) መለያ

•        ሎት - 1 የላቦራቶሪ እቃዎች እና ኬሚካል

•        ሎት - 2 የመኪና ጎማ

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለተፈለገ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የታደሰ ሕጋዊ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።

2.     ተጫራቾች በጨረታለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3.     የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 119 መውሰድ ይችላሉ።

5.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት

•        ሎት- 01 የላብራቶሪ ኬሚካል ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)

•        ሎት 02 የመኪና ጎማ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)

በአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።

6.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ እና በድርጅቱ ማህተም በተደረገበት ፖስታ እያንዳንዱ ፖስታው ላይ ተጽፎ ባህር ዳር ብልጽግና ጽ/ቤት ጎን ከሚገኘው የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማሰገባት ይጠበቅብዎታል።

7.     የጨረታ ሳጥኑ በአስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ወይም ተወካዮች አለመገኘት የጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።

8.     የጨረታው መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

9.     መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ወይም ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 321 6896 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት

ባህር ዳር

 

Save Tender