Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ምርጥ ዘር ድርጅት
  • Address , Phone: 0950265599
  • Website
  • Deadline01 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-01 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

በጌደኦ ዞን ዲላ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት ለምግብነት የሚሆን እና ለምግብነት የማይሆን በቆሎ እና ቦሎቄ ለመሸጥ ሕጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ምርጥ ዘር ድርጅት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 05/2018

 

በጌደኦ ዞን ዲላ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት ለምግብነት የሚሆን እና ለምግብነት የማይሆን በቆሎ እና ቦሎቄ ለመሸጥ ሕጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

የሽያጭ ዓይነት፡- ለምግብነት የማይሆን ቦቆሎ እና ለምግብነት የማይሆን ቦቆሎና ቦሎቄ

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል።

1.       በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባቢነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2.       የሽያጭ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3.       ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

4.       ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በቢሮው ዲላ ምርጥ ዘር ድርጅት| ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.       ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታ። 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከላይ በተባለው ሰዓት ይከፈታል።

6.       በደ/ኢ/ከ/ምርጥ ዘር ድርጅት ስም 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና በማሰራት ከቴክኒክ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት 60 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል።

7.       አሽናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ 05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የእህል ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያዝ በ15 ቀናት ውስጥ ሽያጭ አጠናቀው ለመግዛት ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት።

8.       ለሽያጭ የቀረቡ እህሎች የሚገኙበት አድራሻ በጋሞ ዞን ህብረት ፍሬ ምርጥ ዘር ብኤት እና ህብረት ሥራ ዩኒዬን ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር ግቢ ውስጥ ይገኛል።

9.       ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10.   ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 09 50 26 55 99/ 09 11 02 35 20 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ምርጥ ዘር ድርጅት

Save Tender