በየካ ክ/ከ የወ 01 ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ2ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የተለያዩ መድሀኒቶችን ኬሚካል እና የላብራቶሪ ሬኤጀንቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በየካ ክ/ከ የወ 01 ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከ የወ 01 ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ2ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የተለያዩ መድሀኒቶችን ኬሚካል እና የላብራቶሪ ሬኤጀንቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች
1.የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2/ በመድሀኒት ግዥ አቅራቢነት የተፈቀደበት ከምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ኤጀንሲ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3 ለደንብ ልብስ ስፌት በዘርፉ ለተወዳዳሪነት የተፈቀደበት የምዝገባ ማስረጃቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
4/የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5/ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ከተቋሙ ግዥ ከፍል መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት እና ስም ፤ፊርማናየድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በተቋሙ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
4/ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ብር10000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ በማሰራት ዋናውን ኦርጅናል ከሰነዱ ጋርማቅረብ አለባቸው፡፡
5/ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በይፋ ይከፈታል።
6 የውል ማስከበሪያ የምታሸንፉበትን አጠቃላይ የብር መጠን 10% ሲፒኦ ውል ስትገቡ ማስያዝ አለባችሁ::
7.መድሀኒቶቹ እንዲሁም ሬኤጀንቶቹ በተሰጠው ስፔስፊኬሽንመሰረት መቅረብ አለባቸው ኤክስፓየርድ ዴት ለሚያስፈልጋቸው መድሀኒትም ሆነ ሬኤጀንቶቹ የተመረቱባቸውና ኤክስፓየርድ ጊዜያቸው በግልጽ የሚታይ መሆን አለባቸው የአገልግሎት ጊዜያቸው ቢያንስ አንድ አመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
8 ዋጋ ስትሞሉ አጠቃላይ የሞላችሁትን ዋጋ ድምር ማስቀመጥ ይጠበቅባችኋል::
9/መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
10/ አሽናፊ ተጫራች ውል ከወሰደበት ግዜ ጀምሮ በ7ቀንውስጥመድሀኒቶችና ላብራቶሪ ሪኤጀንቶችእና የህክምና መሳሪያዎች ገቢ ማድረግ አለበት ነገርግን በድርጅቱ መጓተት ምክንያት መ/ቤቱ ስራውን ለመስራት ቢቸገርእርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
11/ጨረታ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60(ለስልሳ ቀን)
አድራሻ - ፈረንሳይ ወደ አርባ አንድ እየሱስ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ከወረዳ oi አስተዳደር ጽ/ቤትአጠገብ፡፡ ለበለጠ መረጃ - ስ.ቁ 0111-548454/0111-549680
የካ ክ/ከ የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ
