Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline17 Nov 2026, 4:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ ወይም 20% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO)
  • opening dateህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት
  • Categories Machinery , Sales, Disposals And Foreclosure , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ሆፕሻይን ትሬዲንግ ኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ከነጀነሬተር በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ከነጀነሬተር ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል::

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ሆፕሻይን ትሬዲንግ ኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ከነጀነሬተር በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ከነጀነሬተር ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል::

ተ.ቁ የተከራዩ ስም የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ዝርዝር መረጃ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የዝግ ጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) ዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ የዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት የጨረታ ሁኔታ
1 ሆፕሻይን ትሬዲንግ
  1. Air compressor (01) psc
  2. Refrigerator Dryer (01) psc
  3. Air purification system (01) set
  4. 95% oxygen generator (01)psc
  5. 99%high purity oxygen generator (01) psc
  6. Oxygen storage tank (01)psc
  7. Buffer thank before oxygen booster/air cooling (psc)
  8. High pressure oxygen booster/air cooling (psc)
  9. Oxygen control box with touch screen controlling system/fixed on 95% oxygen generator diesel generator (01) set
  10. Filling station (01)psc
  11. AESS/auto vent port/system automatically vent the unqualified oxygen/fixed on 95%oxygen generator (01) set
  12. Cylinder with cap/accessory for medical use/ model 40L/ (100) psc
  13. Spare part (01) set
  14. Diesel generator (01) set ናቸው::
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጋሞ ዞን፣ አርባምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ውስጥ ማምረቻ ማሽኖች በሚገኙበት ሼድ 23,250,000 ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን፣ አርባምንጭ ከተማ ህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00 እስከ 6:00 ዝግ ጨረታ

የዝግ ጨረታው መመሪያ

  1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፣ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ ወይም 20% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቃል:: ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዙበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል::
  2. ንብረቱ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ አስ/ር፣ ነጭ ሳር ቀበሌ ውስጥ ማምረቻ ማሽኖች በሚገኙበት ሼድ ውስጥ ነው:: የዝግ ጨረታ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል:: ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት/በሕግ የተወሰነ ታክስ ጨምሮ የሚጠየቁ ማንኛውንም ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል::
  3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል::በዝግ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በዝግ ጨረታ መሳተፍ ይችላል፤
  4. ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመክፈልና የባንኩን የሊዝ ኪራይ መስፈርት በሟሟላት በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃላይ የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል:: ሆኖም ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የዝግ ተጫራች አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል:: ለተሸነፉ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::
  5. ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ አርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክቱ ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል:: የዝግ ጨረታ አሸናፊ ማሽኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል::
  6. የዝግ ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ከለበት ቦታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል::
  7. የዝግ ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኙበት ህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ሎን ወርክአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል::ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር በስልክ ቁጥር 046-181-0606/0303 ደውሎ ማነጋገር ይችላል:: ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዝግ ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት አርባምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ማሽኖቹ በሚገኙበት ቦታ/ሼድ/ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል::ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የዝግ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል::

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank, Arba Minch District, seeks to sell or lease by closed bid a hopchain trading oxygen production plant with generator, including air compressor, dryers, purification system, 95% and 99% oxygen generators, storage tank, booster, control box, filling station, 100 medical cylinders, spare parts and diesel generator, due to the lessee's unpaid lease obligations.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender