ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ለሚገኙ የጤና ተቋማት በድጋፍ መልክ የሚሰጥ የሕፃናት ማሞቂያ (Infant Radiant warmer) በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች/ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሕክምና ዕቃ ግዥ ጨረታ
ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ለሚገኙ የጤና ተቋማት በድጋፍ መልክ የሚሰጥ የሕፃናት ማሞቂያ (Infant Radiant warmer) በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች/ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በመሆኑም በዘርፉ የተሠማራችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፦
- በበጀት ዓመቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ቲን ቁጥር ሰርተፍኬት ያላችሁ፣
- በዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ድርጅቶች/ነጋዴዎች
ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 07 (ሰባት) ቀናት የጨረታ ሠነዱን በብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ቀይት ከሚገኙ የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ከባንክ ሲፒኦ ጋር በፖስታ አሽጎ በማስገባት እንድትወዳደሩ እየጋበዝን ጨረታዉ በ8ኛዉ ቀን በ5:00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ5:30 ሠዓት የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን 8ኛው ቀን በካላንደር የሚዘጋ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳዉቃለን::
ማሳሰቢያ፦ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
ደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር
ጣይቱ ክፍለ ከተማ
ደብረ ብርሃን
ለተጨማሪ መረጃ
ስ.ቁ 011-656-0249 ወይም ኢሜል: procurement@tesfab.org
✨ messages.ai_summary
Tsefah Birhan Children and Family Development Organization seeks suppliers to provide infant radiant warmers as donations to health facilities in Amhara. Eligible bidders need a renewed trade license, VAT and TIN certificates, and proof of good performance.
