Tender Detail

Tender Details


ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለ 2018 ዓ.ም /2026 እ.ኤ.አ የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በቀረቡት ምድብ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ለሁለት አመት የሚቆይ ውል በመፈራረም መስራት ይፈልጋል፡፡

Elilly International Hotel (ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል)


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለ 2018 ዓ.ም /2026 እ.ኤ.አ የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በቀረቡት ምድብ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ለሁለት አመት የሚቆይ ውል በመፈራረም መስራት ይፈልጋል፡፡

የአገልግሎት (የዕቃ) ግዥው አይነቶች ምድብ አንድ፡- የፅህፈት መሳሪያዎችና የቶነር ግዥ፣ ምድብ ሁለት:-የፅዳት ዕቃዎች፣ ምድብ ሶስት፡- የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ምድብ አራት:- የህትመት ውጤቶች፣ ምድብ አምስት:- አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ምድብ ስድስት:- የኬክ ግብዓት፣ ምድብ ሰባት፡- የባልትና እና ቅመማ ቅመም ውጤቶች፣ ምድብ ስምንት፣ ስጋና የስጋ ውጤቶች፣ ምድብ ዘጠኝ፡- አሳ፣ ምድብ አስር፡- ዶሮ እና እንቁለል፣ ምድብ አስራ አንድ፡- የጤፍ ዱቄት፣ ምድብ አስራ ሁለት፡- ግሮሰሪ/የታሸጉ ምግብና የምግብ ግብዓት ግዥ፣ ምድብ አስራ ሶስት፡- የአበባ አቅርቦት ግዥ፣ ምድብ አስራ አራት፡- የቧንቧ ዕቃዎች ግዥ፣ ምድብ አስራ አምስት -የአልኮል መጠጥ አቅርቦት ግዥ፣ ምድብ አስራ ስድስት፡ የቡና አቀርቦት ግዥ፡፡

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::

1.     ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ ቫት ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች እና የሚያቀርቡትን የዋጋ ዝርዝር ከቫት በፊት ባለው ዋጋ ጠቅሰው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::

2.     ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለሚፈልጉት ምድብ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ በኩባንያው ፋይናንስ እና ፕሮኪዩመንት መምሪያ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከስራ አስኪያጅ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች የእቃዎች እና የአገልግሎት ግዥ ሲቀርብ ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል የተፈረመ የጨረታ ሰነዶች ኮፒ የሚነበብ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.     የጨረታ ሰነድ ከገዙ በኋላ በሆቴሉ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ዝርዝሩን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአካል ተገኝተው በም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

5.     ተጫራቾች ለተወዳደሩት ምድብ የጨረታ ማስከበሪያ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ስም 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6.     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ክፍት ሆኖ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆቴሉ የስብሰባ አደራሽ ይከፈታል።

7.     ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል/

ዋናው መ/ቤት ካዛንቺስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ጀነራል ማናጀር ቢሮ ስልክ 0115587777/70

 

ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል

Save Tender