የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ለ 3 አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
የቢሮ ኪራይ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ለ 3 አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም :- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ማያያዝ የሚችሉ እና መብራት ውኃ የተሟላለት መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል በአስተዳደሩ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው የከፍሎች ብዛት እና ስፔስፊኬሽን መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን 8፡30 በዋናው መስሪያ ቤት ሲሆን አሸናፊው ሲለይ ውል ለመፈጸም ዝግጁ የሆኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለኪራዩ የሚቀርበው ዋጋ VAT ማካተትና ያለማካተቱን መገለጽ ይኖርበታል፡፡
የሪጅን ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን ለቢሮ የሚሆነውን ቦታ እና መረጃ የመስጠት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
ከአስፋልት ወይም ከዋናው መንገድ ገባ ያለ ከሆነ 500 ሜትር መብለጥ የለበትም፡፡ ከዋናው መንገድ ገባ ያለ ከሆነ እስከ ስፍራው ድረስ የአስፋልት፣ የጠጠር ወይም የኮብል እስቶን ንጣፍ መንገድ ያለውና በቂ የጥበቃ ክፍሎች ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡
አድራሻ፡- ድሬዳዋ ከተማ ገንደ ቆሬ ፎዚያ ሕንጻ ድሬዳዋ ጤና ቢሮ አጠገብ
ስልክ:- 0251124735 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
