Tender Detail

Tender Details

  • Company አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ጨው በረንዳ በሚወስደው መንገድ ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 400 ሜትር ርቀት ላይ ወረዳ 6 አስተዳደር ግቢ ውስጥ ሁለተኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2-73-58-85
  • Website
  • Deadline16 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-16 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ውስጥ የሚገኘው የወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት 2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለ2018 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ውስጥ የሚገኘው የወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት 2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለ2018 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

•        ሎት 1 የደንብ ልብስ = 6,854.96 ብር

•        ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች = 8,491.35 ብር

•        ሎት 3 የፅዳት እቃዎች = 22,000.00 ብር

•        ሎት 4 ሌሎች አላቂ እቃዎች = 10,271.03 ብር

ተጫራቾች ከሚጫረቱበት እቃ ጋር ግንኙነት ያለው የዘመኑን ግብር የተከፈለ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው በጨረታው ተካፋይ መሆን እንደሚችሉ የሚያመለከት ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የአቅራቢ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት ከሚጫረታቸው ሰነዶች ጋር አባሪ መሆን ይኖርበታል፡፡ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ቢሮ 2ኛ ፎቅ ላይ ፋይናንስ ፅ/ቤት በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡

1.     ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ለፋይናንስ ፅ/ቤት በሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

2.     የጨረታው ሰነድ ሲገባ ናሙና አብሮ መቅረብ አለበት ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡበት ሰነድ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው

3.     ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ከመስሪያ ቤታችን ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ ዋጋውን 10% ዋጋ ማስያዝ ይኖርበታል፤ በተጨማሪ የአሸናፊውን እቃ በ10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ግዴታ አለበት ይህ ባይሆን ግን ለጨረታው የተያዘውን በሲፒኦ /CPO/ ዋጋ በቀጥታ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡

4.     ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይዘጋል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

5.     መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

6.     በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አካላት በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ብቻ መወዳደር ከፈለጉ ህጋዊ ማስረጃ ሲያቀርቡ ሰነድ ወስደው መወዳደር ይችላሉ፡፡

7.     በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡

8.     ጽ/ቤቱ ከውል በፊት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ ከውል በኋላ 25% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9.     አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡

10. አሸናፊው ያሸነፈባቸውን ንብረቶች የወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተጫራቾች የአንዱ ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ አለበት ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት (እንዳካተተ) ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

12. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚያስገባው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡

 

አድራሻ፡- ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ጨው በረንዳ በሚወስደው መንገድ ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 400 ሜትር ርቀት ላይ ወረዳ 6 አስተዳደር ግቢ ውስጥ ሁለተኛ ፎቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011-2-73-58-85 ወይም 0112-77-48-00

 

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት

Save Tender