Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ
  • Address ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከገነት ሆቴል ወደ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115536456
  • Website
  • Deadline17 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price250.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-18 00:00:00
  • Categories Chemicals And Reagents , Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Pharmaceutical Products , Stationery Materials

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ፡-

1.     መድኃኒቶች እና ሬጀንቶች

2.     የደንብ ልብሶች

3.     የጽዳት እቃዎች

4.     ተለያዩ የጽህፈት እቃዎች

5.     እድሳት እና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ማንኛውም ሕጋዊ የንግድ ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 በሥራ ሰዓት በመቅረብ እና በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል እና የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

1.     በግብር ከፋይነት የተመዘገቡ መሆነቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2.     የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ መያዣ የሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ ሲፒኦ (CPO) ኮፒው ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

4.     ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት አስፈላጊውን የትብብር ደብዳቤ ለማወዳደር የሚከፈተው ፖስታ ማለትም በኮፒው ውስጥ በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

5.     አሸናፊው የንግድ ድርጅት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅበታል።

6.     ኦርጅናል ፖስታ በጨረታ ማወዳደሪያ ወቅት አይከፈትም፡፡

7.     ተጫራቾች በአቅራቢዎች ድረ-ገጽ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

8.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዝርዝር ጤና ጣቢያው ባቀረበው የዋጋ ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት እና እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋጋውን እና ኮፒውን በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።በተጨማሪም ቴከኒካል ሰነድ ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ በድጋሚ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለበት።

9.     ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሁሉም ተጫራቾች ናሙና ከጨረታው ሰነድ በጋራ ማቅረብ አለባቸው።

10. ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።

11. ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችለው ከንግድ ፈቃድ ጋር ተያያዥነት ባላቸው አቅርቦቶች አገልግሎቶች ላይ ብቻ ነው።

 

ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የሚቀርቡት ዋጋዎች ተጨማሪ እሴት ታክስን /ተርን ኦቨርታክስን ያካተቱ መሆን አለባቸው።

አድራሻ:- “ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከገነት ሆቴል ወደ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0115536456/0115156192 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender