የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለወረዳዉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለወረዳዉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ
• ሎት1፡- የደንብ ልብስ
• ሎት2፡- የፅህፈት መሳሪያዎችና
• ሎት3፡- የጽዳት እቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዚህ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች/ሕጋዊ ውክልና ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት
የምታሟሉ በአካል ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እንገልፃለን።
በጨረታው ለመሳተፍ /ለመወዳደር/ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለዉ፤
2. የ2018 የመንግስት ግብር የከፈለ ክሊራንስ ያለዉ እና የ2018 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
3. VAT ተመዝጋቢ የሆነ፤
4. በመንግስት ግዥዎች በአቅራቢነት የተመዘገበበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
5. የተፈለገዉን የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችል፤
6. በተባለበት ቦታና ቀን እቃዉን ቢሮ ድረስ ማቅረብ የሚችል፤
7. በስራና ከህሎት የተደራጃችሁ ኢንተርፕራዙ በተደራጁበት የስራ ዘርፍ ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚያደረግላቸዉ ሲሆን ይህም የሚደረገዉ ከአደራጃቸዉ ጽ/ቤት ኃላፊ ብቻ በተፈረመ የድጋፍ ዳብዳቤ ይሆናል። ከስራ ዘርፉ ዉጭ ለሆኑት እንደማንኛዉም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል።
8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር በእያንዳንዱ ሎት 400 (አራት መቶ ብር) ከፍሎ መግዛት የሚችል፧
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ሎት 5,000 (አምስት ሺህ) የኢትዮጵያ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበርያ ያላስያዘ በጨረታው ሰነድ የመጀመርያ (ቅድመ) ምርመራ ውድቅ ይሆናል።
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ንብረት ክፍል/ ድረስ መጓጓዣና የመገጣጠሚያ ዋጋ አካትተዉ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
11. የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘዉ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ አርጅናልና ኮፒ ከጨረታዉ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርበታል።
12. የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ለሚ ኩራ/ክ/ከ/ወ/04/4/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 302 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ ።
13. ጨረታውን ለመገምንም በሥራ ላይ የሚዉሉትን ዘዴዎች ለዚሁ ግምገማ የሚያገለግሉትን መስፈርቶች እና እያንዳንዱ መስፈርት የሚኖረዉን ድርሻ እንዱሁም ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆነ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በግምግማ እኩል በሆኑ ጊዜ አሸናፊን ለመለየት በግዥ መመረያዉ መሰረት የሚለይ ይሆናል።
14. ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታዉ እራሳቸውን ማግለል አይቻልም።
15. የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ግዥዉን 10% በብር /ሕጋዊ CPO ማስያዝ የሚችል።
16. የጨረታ ሰነድ ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሻሌ 40/60 ኮንዶሚንኒየም አለፍ ብሎ ቃጥላ ማርያም መግቢያ በግምት 100 ሜትር ገባ ብሎ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 302 መግዛት ይቻላል።
17. ጨረታው በአስራ አንደኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቹ/ህጋዊ ወኪል/ በተገኘበት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ ህጋዊ ወኪሉ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተጽዕኖ አያመጣም።
18. ውድድሩን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ዉድድሩን ማሸነፉ ከታወቀ ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ በአካል ቀርቦ የዉል ስምምነት መፈረም አለበት ።
19. ናሙና ለተጠየቀባቸው የዕቃ አይነቶች ተወዳዳሪዎች ምንም አይነት መለያ (ምልክት ያልተደረገበት ለእያንዳንዱ እቃ አንድ ናሙና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ውድድሩን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ይሆናል።
አድራሻ:- ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በሻሌ 40/60 ኮንዶሚኒየም አለፍ ብሎ ቃጥላ ማርያም መግቢያ 100ሜ ገባ ብሎ።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት
