የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ 103ኛ ኮር ጠ/መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ዕዝ ጠ/መምሪያ የ103ኛ ኮር መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ 103ኛ ኮር ጠ/መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. የአላቂ የፅህፈት መሳሪያ
2. የተሰጠና የፅህፈት እቃ ግዥ
3. የህሙማን ማገገሚያ ቀለብ
4. የፅዳት እቃዎች ግዥ
5. የመለዋወጫ እቃዎች
6. የጀነሬተር መለዋወጫ የዳቦ ማሽን መለዋወጫ እቃ ግዥ
በዚህም መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የቫት ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸውን ይጋብዛል።
ተጫራቾቹ የጨረታውን ዝርዝር መመሪያና ዝርዝር ሰነድ የያዘ ለተራ ቁጥር 01-06 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ/ ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ግምቢ የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳደር ጊቢ የምገኘው በ103ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ፋይናንስ ቢሮ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቀን ጨረታው የካቲት 10/06/2018 ከሰዓት 8፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 9፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻ በተገኙበት ይከፈታል። መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0919079321/0917934023
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ 103ኛ ኮር ጠ/መምሪያ
