Tender Detail

Tender Details


የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ጽ/ቤቶች የሚውል አላቂ የቢሮ እቃዎች፤ የደንብ ልብሶች እና የፅዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የየካ ከ/ከተማ የወረዳ12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ጽ/ቤቶች የሚውል አላቂ የቢሮ እቃዎች፤ የደንብ ልብሶች እና የፅዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። እንዲሁም የአገልግሎት ግዥዎችን ማለትም የመስተንግዶ ግዥ፣ የህትመት ስራዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የጭነት አገልግሎት እና የዲኮር ስራዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። መወዳደር የምትፈልጉ-

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የታደሰ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ እና በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ለመሳተፍ እንዲችሉ የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣቸው የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ እና በተጨማሪ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ አለባቸው)። የሚቀርበው ሰነድ የሚታይ መሆን አለበት።

2.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት መሆኑን እየገለፅን በ 11 ኛው ቀን ከቀኑ በ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከታች በተገለፀው አድራሻ ጨረታው በሚዘጋበት ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ። ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።

3.     ተጫራቾች የጨረታውን የማይመለስ የሰነድ መሸጫ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) በየሎቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይበባንክ በተረጋገጠ CPO ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃ አይነት የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን ሲያስገቡ ከአገልግሎት ግዥ በስተቀር ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ያለ ናሙና የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

6.     አሸናፊ ድርጅቶች ውል ስትዋዋሉ የውል ማስከበሪያ 10% ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7.     አድራሻችን ኮተቤ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ ወይም ሰንሻይን መንደር ፊት ለፊት ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ዋ/የስራ ሂደት ክፍል ሲሆን

 

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0118931691 በመደወል የሚፈልጉትን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡- ተቋሙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender