የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002 /2018 ዓ.ም
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1፡ የደንብ ልብስ፤ ሎት2፡ የፅህፈት ዕቃ፣ ሎት3: የፅዳት ዕቃ፣ ሎት4: ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ሎት6: የህትመት ዕቃ፤ ሎት 7: የድንኳንና ዲኮር መስል ዕቃዎች ኪራይ፤ ሎት8፡ የመስተንግዶ አገልግሎት፤ ሎት9፤ የግብርና ዕቃዎች ሎትıo.የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ
1. በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣የንግድ ስም ምዝገባ/ምስከር ወረቀት/፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና በንግድ ሥራ ፍቃድ በጀርባው ያለውን የሥራ ዘርፍ የተገለፀበትን ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ እና የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ጨምሮ መሆኑን መግለጫ መስጠት አለባቸው
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ማቅረብ የሚችሉ
4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00ብር /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 02 ፋ/ጽ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ከፍል መግዛት ይችላሉ።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሁሉም ሎት ሃያ ሽህ(20,000) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ ያቅራቢ ማህተም እና በዋጋ ማቅረቢያው ዝርዝር ላይ ዝርዝሩን የሞላው ኃላፊ በእያንዳንዱ ዋጋ በተሞላበት የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ በመፈረም ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀውን የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ዋጋ ማቅረቢያ ሲያቀርቡ አርጅናል ደረጃውን የጠበቀና ናሙናውን በ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ፋ/ጽ/ቤት ለግዥ ከፍል ማስረከብ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች ያሸነፉአቸውን ዕቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን በቀረበው ናሙና መሰረት የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
9. ጨረታው የሚዘጋበት በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ላይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ላይ ይሆናል።
10. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈፃፀም ውል ማስከበሪያ ለአሸነፉበት ዕቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው፡፡
11. ናሙና የሚያስፈልጉ እቃዎችን በተባለበት ቀን ውስጥ ማስረከብ አለባችሁ፡፡
12. ከፍያው የሚፈፀመው ለሚያቀርቡት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ለፋ/ጽ/ቤት ንብረት ከፍል ሲያስረከቡና የቀረበው ዕቃ በናሙና መሰረት በጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
13. በጨረታ ሰነዱ ላይ የዋጋ ስርዝ ድልዝ እና ጽ/ቤቱ የሠጠውን እስፔስፊኬሽን መሰረዝ የለበትም።
14. የጨረታ ማስረከቢያና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስከ/ዘርፍ/ የሚገልጽ ደብዳቤ መቅረብ አለበት፡፡
15. ዋስትና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አሸናፊው ለለአመት የሚቆይ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል
16. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ቢበዛ ለ60 ቀናት ብቻ ነው።
17. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ ትከከል መሙላት ይኖርባችኋል።
18. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር +251118668057 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ፋ/ጽ/ቤት ከሀያት ወደ ጣፎ የሚወስደው መንገድ ብርሀን ባንክ ያለበት ህንጻ/3ኛፎቅ አካባቢው ልዩ ቦታ ክብርዳማና
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
