ሜትሮፖሊታን ታበርናክል ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 1, 2025 እስከ ዲሴምበር 31, 2025 ያለውን ሂሳቡን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ የሃገር ውስጥ ኦዲት ድርጅቶችን አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
ሜትሮፖሊታን ታበርናክል ኢትዮጵያ
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
ሜትሮፖሊታን ታበርናክል ኢትዮጵያ በኢፌዴሪ በሲቪል ማህበራት ኤጄንሲ የተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅቱ እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 1, 2025 እስከ ዲሴምበር 31, 2025 ያለውን ሂሳቡን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ የሃገር ውስጥ ኦዲት ድርጅቶችን አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር አመልካቶች፣
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ፣
2. የሙያ ማረጋገጫ ያለውና በAABE የምስክር ወረቀት የተሰጠው፣
3. የቲን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ኮፒ፣
4. የግብር ከፋይ ማረጋገጫ ኮፒ፣
5. ከNGOs ጋር ቀደም ያለ የኦዲት ተሞክሮ እና በIPAS ላይ የተመሰረተ የሂሳብ አያያዝ መረጃ ማቅረብ የሚችል፣
6. የኦዲት ሥራውን የመጨረሻ ሪፖርት ማቅረቢያ ቀኑን የሚያሳውቅ፣
7. ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ተጨማሪ መረጃዎች ማቅረብ የሚችል የኦዲት ድርጅት የአገልግሎት ክፍያውን ቫትን ጨምሮ በመጥቀስ የሚወዳደሩበትን መረጃዎች በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት አስር የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ቢሾፍቱ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በአካል ማቅረብ ይችላሉ፡፡
የበጀት አመቱን የሂሳብ መዛግብትና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ቢሾፍቱ በድርጅቱ ጽ/ቤት በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0911 67 38 63 እና 0911 79 57 04 መደወልና መረጃ ማግኘት ይቻላል።
ሜትሮፖሊታን ታበርናክል ኢትዮጵያ
