Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የቅዱስ ላሊበላ ጠቅላላ ሆስፒታል የተለያዩ ግብአቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የቅዱስ ላሊበላ ጠቅላላ ሆስፒታል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የቅዱስ ላሊበላ ጠቅላላ ሆስፒታል የተለያዩ ግብአቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። እነዚህም የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃ፣ የተለያዩ ህትመቶች፣ የመኪና እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚ እቃና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1.     በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሰረት በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ሰርተፊኬት ያላቸው

2.     ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ ይህን መረጃ ማቅረብ የሚችሉና የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፖስታ ውስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.     ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የቅዱስ ላሊበላ ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አሰ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር46 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለምትሞሉት ማስከበሪያ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታው ላይ በተመሰረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የመ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ ላይ በማስያዝ ደረሰኙ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት። የተሞላው ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ከ40 ቀናት በላይ መሆን አለበት። ከ40 ቀናት ያነሰ የሚቀርቡ ተጫራቾች ቢኖሩ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይሆናሉ።

5.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም የጨረታ ሰነዶች በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4፡15 ሰአት ይከፈታል።

6.     ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።

7.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉን በፖስታ ወይም በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8.     ፅ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው የወጭ በጀቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚገባውን እቃ ብዛት በግዥ ትእዛዝ ወቅት 20% /ሃያ በመቶ/ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.     አሸናፊው አካል እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት የቅዱስ ላሊበላ ጠቅላላ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

10. በጨረታ ግምገማ ውጤት ቅር የተሰኘ ተጫራች ውጤቱ በተገለፀለት በ5 የስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ካለው ጨረታውን ላወጣው ግዥ ፈፃሚ አካል በፅሁፍ ሊያቀርብ ይችላል።

11. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡበት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

12. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም። ውድድሩ በሎት ምድብ ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለበት፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሌላው መ/ቤቱ ካዘጋጀው ሰነድ ውጭ መሙላት አይቻልም። ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። በተለያየ እስክሪቢቶ መሞላት የለበትም፡፡

14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 46 በመገኘት ማነጋገር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን። በአካል በመገኘት እና በስልክ ቁጥራችን 0333360101 በመደወል መረጃ ማግኝት ትችላላችሁ።

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የቅዱስ ላሊበላ ጠቅላላ ሆስፒታል

 

Save Tender