በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የወ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት በ2016 ዓ.ም በከተማው ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ቋሚ አላቂ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የወ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት በ2016 ዓ.ም በከተማው ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
• ሎት 1- የጽህፈት መሳሪያዎች
• ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች
ሎት3 - ቋሚ አላቂ እቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ይጋበዛል።
1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
2. የግዥ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
4. የሚገዛውን የእቃ ዝርዝር መገለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 በመሄድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ ፣
6. የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እና በየሎቶቹ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች በየሎቶቹ የጨረታ ሰነዱን አሪጂናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በማሸግ ወረኢሉ ከ/አስ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል።
8. ጨረታው በሎት ወይም በጥቅል ድምር ስለሆነ ያልተሞላ አይተም ካለ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል።
9. በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ መደረግ አለበት።
10. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተ በኋላ ለ40 ቀናት ይሆናል።
11. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ከመክፈቻው 5 ቀን በፊት በአካል ወይም በስ.ቁ 0919972162 /0914082813 0920271833 /ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡
12. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ማሳሰቢያ
• እቃዎች መ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት መቅረብ አለባቸው፡፡
• ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፤
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የወ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት
