በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ: - ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 3 ሕትመቶች ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፤
የሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ብሄራዊ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ: - ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 3 ሕትመቶች ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፤
1. ተጫራቾች ህጋዊ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
2. በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመከፈል ከ 15/5/2018 ዓ.ም እስከ 29/5/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
3. የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ እና ዋጋው መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልፅ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
4. የጨረታ ሳጥኑ በቀን 30/5/2018 ቀን 4፡01 ሰአት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ 30/5/2018 በቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች በየሚሰጥ እንደተጫራቾቹ ምርጫ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በጥሬ ገንዘብ /cpo/ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች አሸናፊ ውል ከፈፀመ በኋላ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊው ድርጅት ውል ፈፅሞ 10%የውል ማስከበሪያ እንዳስያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ይመለስለታል።
7. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀኖች ውስጥ ውል መግባት ይጠበቅበታል። ያስያዘው 10% የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መጋዘን ካስረከበ ከ30 ቀናት በኋላ ይመለስለታል።
8. በሎት 2 የምትወዳደሩ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
9. ፍርድ ቤቱ የሚገዛውን እቃ ብዛት 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
11. ተጨማሪ መረጃዎችንና የጨረታ ሰነድ በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥፋይ/ንብ/አስ/ድን ቢሮ ቁጥር12 ማግኘት ይችላሉ።
12. ውድድሩ የሚደረገው በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዋጋ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 033-444-0341/0030 ይደውሉ ማሳሰቢያ፡ የሚከፈትበት ቀን በአል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው በስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
የሰሜን ሸዋ ዞን አንጾኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት መኮይ
